Loading
ማዕበሉን ፡ በስልጣን ፡ የሚገስጽልኝ ዞር ፡ በል ፡ የሚልልኝ አባት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ አባት ፡ አለኝ (፪x) ረዳት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ ረዳት ፡ አለኝ (፪x) ከእናት ፡ ካባቴም ፡ በላይ ፡ ለኔ ፡ ራርተህ ፡ ስላየሁ (አሃሃ ፡ አሃ) እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እላለሁ ስደክም ፡ አበርትተህ ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀባህ (አሃሃ ፡ አሃ) ጽዋዬም ፡ ተረፈልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ ጌታ ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ ፡ ውዴ ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ (፪x) ሰው ፡ ቢጥል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያነሳል (ሰው ፡ ቢጥል) ሰው ፡ ቢጥል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያነሳል ከብሮ ፡ ያከብራል ፡ ከፍ ፡ ያደርጋል ሰው ፡ ቢጥል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያነሳል (ሰው ፡ ቢጥል) (፪x) እንቅልፍ ፡ እንደያዘው ፡ እንደተኛ ፡ ሰው (፪x) መስሎኝ ፡ ነበር ፡ እኔስ ፡ ግድ ፡ ማይለው (፪x) ኧረ ፡ ይሄስ ፡ ሰው ፡ ሃይለኛ ፡ ነው ፡ ተነሳና ፡ ዞር ፡ በል አለው ኧረ ፡ ይሄስ ፡ ሰው ፡ ሃይለኛ ፡ ነው ፡ ተነሳና ፡ ጸጥ ፡ በል ፡ አለው አዝ፦ማዕበሉን ፡ በስልጣን ፡ የሚገስጽልኝ ዞር ፡ በል ፡ የሚልልኝ አባት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ አባት ፡ አለኝ (፪x) ረዳት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ ረዳት ፡ አለኝ (፪x) የምስኪን ፡ ወዳጅ ፡ ሆነህ ፡ በጐጆዬ ፡ ውስጥ ፡ ገባህ (አሃሃ ፡ አሃ) የዘመመው ፡ ቤቴ ፡ ይኸው ፡ ባንተ ፡ ቀና ታዲያ ፡ ልዘምር ፡ እንጂ ፡ ለምን ፡ ላጉረምርም (አሃሃ ፡ አሃ) በጐጆዬ ፡ ውስጥ ፡ ያለው ፡ ኢየሱስ ፡ ይክበር ፡ ውድዬ ይክበር ጌትዬ ፡ ይክበር ፡ ወድዬ ፡ ይክበር አዝ፦ማዕበሉን ፡ በስልጣን ፡ የሚገስጽልኝ ዞር ፡ በል ፡ የሚልልኝ አባት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ አባት ፡ አለኝ (፪x) ረዳት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ ረዳት ፡ አለኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.