Loading
ክብሬ ፡ ጌጤ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ሽልማቴ አጠገቤ ፡ ሳይህ ፡ ወደድኩህ ፡ አባቴ ደጅ ፡ አላስጠናኸኝ ፡ አንተን ፡ ለማግኘት ሳልፈልግህ ፡ መጥተህ ፡ ገባህ ፡ ከእኔ ፡ ቤት አዝ፦ አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጌ ጌታን ፡ ተማምኜ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ አጥቼ (፪x) ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ አጥቼ (፬x) የጠበኩት ፡ ሁሉ ፡ ያሰብኩት ፡ ባይሞላ አንተ ፡ ካለህልኝ ፡ ምነው ፡ ባይበላ ተስፋዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሙጥኝ ፡ እላለሁ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ኖሮ ፡ ሞት ፡ ለእኔ ፡ ክብር ፡ ነው ትምክቴ ፡ ነህ ፡ በአንተ ፡ እታመናለሁ የትናንቱን ፡ እንዴት ፡ ረሳዋለሁ ተንከባክበህ ፡ አሳድገኸኛል ለነገዬ ፡ ምንስ ፡ ያስፈራኛል (፪x) ዓለም ፡ ሁሉ ፡ ክዶህ ፡ ብቻዬን ፡ ብቀር እኔስ ፡ አለኝ ፡ ለእኔ ፡ ሕያው ፡ ምስክር የልጅነቴ ፡ አምላክ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆነሃል ጐጆዬ ፡ ስትገባ ፡ ሙሉ ፡ ዓይኔ ፡ አይቶሃል አዝ፦ አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጌ ጌታን ፡ ተማምኜ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ አጥቼ (፪x) ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ አጥቼ (፬x) የአጀበ ፡ ሲበተን ፡ ጐኔ ፡ የነበረው ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ ወረት ፡ ሲቀይረው አንዱ ፡ እንደ ፡ ሺህ ፡ ሆነ ፡ ቤቴን ፡ አድምቀሃል የጐደለኝ ፡ የለም ፡ ወዳጄ ፡ ሆነሃል
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.