Loading
ኢየሱስ ፡ ስለእኛ ፡ መስቀል ፡ ተሸክሞ ቀራንዮ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ በጅራፍ ፡ ተገርፎ ጐልጐታ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ በግፍ ፡ ተሰቀለ እንደጅራት ፡ ደሙ ፡ በሜዳ ፡ ፈሰሰ ሞተ ፡ ተቀበረ ፡ ተስፋ ፡ የለው ፡ ብለው ተከታይ ፡ ልጆቹ ፡ በሃዘን ፡ ተመተው አዳኛችን ፡ ኢየሱስ ፡ በክብር ፡ ተነሳ ከሙታን ፡ አለት ፡ ውስጥ ፡ እኛንም ፡ አስነሳን በትንሳኤው ፡ ኃይል ፡ ማሸነፍ ፡ ያገኙ ከሞት ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ የተሸጋገሩ የከበረ ፡ ሠማይ ፡ ይጠብቃቸዋል መኖሪያቸው ፡ ሁሌ ፡ በእዚያ ፡ ይሆናል ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ በጌታችን ፡ ደም በደል ፡ ተሰረየ ፡ በመሲሁ ፡ ደም የዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አይታሰብም ክቡር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ለመድሃኒዓለም የዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አያገኘንም ክቡር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ለመድኃኒዓለም ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ በመሲሁ ፡ ደም በደል ፡ ተሰረየ ፡ በጌታችን ፡ ደም የዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አይታሰብም ክቡር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ለመድሃኒዓለም (፪x) አማኑኤል ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፬x) መዳናችን ፡ በእርሱ ፡ ነው (፫x) አማኑኤል ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፬x) መዳናችን ፡ በእርሱ ፡ ነው (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.