Loading
አዝ፦ አርበኛ ፡ ነኝ (፪x) ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ ጌታም ፡ አድርጐኛል ፡ የእውነት ፡ ሰራተኛ (፪x) አልፈራ ፡ አልደነግጥ ፡ ልቤም ፡ አይሸበር ጌታ ፡ ፍርሃቴን ፡ አድርጐታል ፡ ሰበር (አድርጐታል ፡ ሰበር) ጉልበታም ፡ መንፈሱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ተለቋል ጠላቴ ፡ ይህን ፡ አይቶ ፡ ሁሌ ፡ ያንዣብባል ይዙር ፡ ያንዣብ ፡ እንጂ ፡ ምኔን ፡ ያገኘዋል (ይዙር ፡ ያንዣብ ፡ እንጂ ፡ ምኔን ፡ ያገኘዋል) እኔን ፡ ሊነካ ፡ ሲል ፡ እሳት ፡ ይቀድመዋል (፪x) አዝ፦ አርበኛ ፡ ነኝ (፪x) ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ ጌታም ፡ አድርጐኛል ፡ የእውነት ፡ ሰራተኛ (፪x) ቅጥሬ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ጦር ፡ ደሞዜ ፡ በሰማይ ይሄ ፡ ስለሆነ ፡ ምንም ፡ ምንም ፡ አላይ (ምንም ፡ ምንም ፡ አላይ) በሃይል ፡ ተሞልቼ ፡ በብርቱ ፡ እዋጋለሁ ያዘዘኝን ፡ ጌታ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ላሰኘው አዝ፦ አርበኛ ፡ ነኝ (፪x) ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ ጌታም ፡ አድርጐኛል ፡ የእውነት ፡ ሰራተኛ (፪x) በጠቅላዩ ፡ ገዤ ፡ በኢየሱስ ፡ ታዝዤ ወደጠላት ፡ መንደር ፡ በመንፈስ ፡ ገስግሼ (በመንፈስ ፡ ገስግሼ) ጉድ ፡ ሳልሰራ ፡ አልመጣም ፡ በፍፁም ፡ በባዶ አየዋለሁ ፡ ጠላት ፡ በእሳት ፡ ቆስሎ ፡ ነዶ ይዙር ፡ ያንዣብ ፡ እንጂ ፡ ምኔን ፡ ያገኘዋል (ይዙር ፡ ያንዣብ ፡ እንጂ ፡ ምኔን ፡ ያገኘዋል) እኔን ፡ ሊነካ ፡ ሲል ፡ እሳት ፡ ይቀድመዋል (፪x) ደግሞ ፡ ለጠላቴ ፡ እድል ፡ ፈንታ ፡ አልሰጥም ከደሊላ ፡ ጭን ፡ ላይ ፡ ተኝቼ ፡ አልገኝም (አልገኝም) የጌታዬ ፡ መንፈስ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ስላለ እንደወደደው ፡ ያድርገኝ ፡ እርሱ ፡ እንደፈለገ አዝ፦ አርበኛ ፡ ነኝ (፪x) ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ ጌታም ፡ አድርጐኛል ፡ የእውነት ፡ ሰራተኛ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.