Loading
ጌታ ፡ ፈጣሪዬ ፡ ስለ ፡ አፈጣጠሬ ስለሚያስደንቀው ፡ ስለ ፡ አካል ፡ ክፍሌ ላመሰግንህ ፡ እፈልጋለው ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ሆኜ ፡ ተፈጥሪያለው [፪X] ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ [፪X] የማመስገኛ ፡ ምክንያት ፡ ከሆነ ከቁጥር ፡ በላይ ፡ እኔ ፡ ጋር ፡ አለ እግሬ ፡ ሲራመድ ፡ ሚዛን ፡ ጠብቆ ዓይኔም ፡ ሲያይልኝ ፡ ቅርብም ፡ አርቆ በራስ ፡ ቅሌ ፡ ላይ ፡ ሲበቅል ፡ ፀጉሬ ጣቶቼ ፡ ላይ ፡ ሲያድግ ፡ ጥፍሬ ውበት ፡ አላቸው ፡ በየቦታቸው ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራሃቸው [፪X] ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ [፪X] ሰው ፡ ሰውን ፡ ቢሰራው ቢያበጀው ፡ እስትንፋስ ፡ ቢሰጠው የሚከፍለው ፡ አጥቶ ሁሉም ፡ ሰው ፡ መኖር ፡ በተሳነው ይተመን ፡ ቢባል ፡ በዋጋ ፡ የአካል ፡ ክፍሌ በዓለም ፡ ያለው ፡ ሃብት ፡ በሙሉ ፡ አይመጥን ፡ ለኔ እንዃን ፡ ሁሉንም ፡ ይቅርና ፡ አንዱንስ ፡ እንኳ መፍጠር ፡ ያልቻለው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ እንዴት ፡ ይመካ ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ [፪X] በሚጥም ፡ ዜማ ፡ የሚያዜመው ፡ የአንተን ፡ ዝማሬ ገንዘብ ፡ ሊገዛው ፡ አይችል ፡ ይህ ፡ አንደበቴ [፪X] ጌታ ፡ ፈጣሪዬ ፡ ስለ ፡ አፈጣጠሬ ስለሚያስደንቀው ፡ ስለ ፡ አካል ፡ ክፍሌ ላመሰግንህ ፡ እፈልጋለው ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ሆኜ ፡ ተፈጥሪያለው [፪X] ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ [፪X]
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.