Loading
አመልክሃለሁ (፬x) ትምክቴ ፡ ነህ ፡ የኩራቴ ፡ ጥግ ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ ፡ ማዕረግ (፪x) አሁንም ፡ ላምልክህ ፡ ላምልክህ (፬x) የጨዋታዬ ፡ መነሻ ፡ ርሶ ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አልፎም ፡ ንኡሱ የዕድሜ ፡ ልኬ ፡ ስብከት ፡ ትምህርት ኩራቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የማልታክትህ ስነሳም ፡ በአንተ ፡ ስቀመጥ ፡ በአንተ ስጀምር ፡ በአንተ ፡ ስጨርስ ፡ በአንተ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ስብከት ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ትምህርት (፪x) አንተን ፡ አደብዝዞ ፡ አዜብ ፡ የሚሆንብኝ የፍርህን ፡ ምስል ፡ የሚያጨልምብኝ ይውጣ ፡ ከጓዳዬ ፡ በእሳት ፡ መጥረጊያ አልፎ ፡ አይውጠኝም ፡ የሥምህን ፡ መዝጊያ ኢየሱስ ፡ የሚለውን ፡ እርስ ፡ አልቀይርም በሚጠፋው ፡ ዓለም ፡ ጌጤን ፡ አልሸፍንም ልቤ ፡ አይሸፍትም ፡ ፍቅርህ ፡ ላይ ፡ ዘምኖ ይህ ፡ ልብ ፡ ብሶበታል ፡ መሮጥ ፡ አንተን ፡ ብሎ ስነሳም ፡ በአንተ ፡ ስቀመጥ ፡ በአንተ ስጀምር ፡ በአንተ ፡ ስጨርስ ፡ በአንተ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ስብከት ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ትምህርት (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.