Loading
ፀሐይ ፡ ፈነጠቀች ፡ ደረሰ ፡ ጠዋቱ ድምጼም ፡ ያስተጋባ ፡ የገደል ፡ ማሚቱ እግዚአብሔርን ፡ ልጥራ ፡ በውዳሴ ፡ አሃዱ ይነጫነጭ ፡ ጠላት ፡ ያው ፡ እንደልማዱ (፫x) ተመቻችቶ ፡ ነበር ፡ እርስቱን ፡ አስፍቶ ዝምታዬ ፡ ጣፍጦት ፡ ሲቧርቅ ፡ ሰንብቶ ስለቴ ፡ ደርሶልኝ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ብዘምር ሽብር ፡ ተፈጠረ ፡ በዲያብሎስ ፡ ቅጥር በማለዳ ፡ ዜማ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከበረ ክፋት ፡ ሸራቢው ፡ ግን ፡ ዲያብሎስ ፡ አፈረ እርሱ ፡ እንዳሻው ፡ ይሁን ፡ የሲኦሉ ፡ ሲሳይ እኔ ፡ ግን ፡ ልዘምር ፡ ላለው ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ በክረምት ፡ በበጋ ፡ በህመም ፡ በጤና በክብር ፡ በውርደት ፡ በድል ፡ እንደገና በማግኘት ፡ በማጣት ፡ በትርፍ ፡ በኪሳራ ስንቱን ፡ አቋርጠናል ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ ፀሐይ ፡ ፈነጠቀች ፡ ደረሰ ፡ ጠዋቱ ድምጼም ፡ ያስተጋባ ፡ የገደል ፡ ማሚቱ እግዚአብሔርን ፡ ልጥራ ፡ በውዳሴ ፡ አሃዱ ይነጫነጭ ፡ ጠላት ፡ ያው ፡ እንደልማዱ (፫x) ዙሬያየን ፡ የማየው ፡ እልልም ፡ ባያሰኝ የክብሩን ፡ መስዋእት ፡ ልነፍግ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ በዘመነ ፡ መልካም ፡ ወይ ፡ ዘመን ፡ ቁዛሜ እወድሰዋለሁ ፡ በሰዎች ፡ ፊት ፡ ቆሜ ጆሯችንን ፡ ሰርቆ ፡ ሹክ ፡ የሚለን ፡ ጠላት ሰፍሮ ፡ ትከሻችን ፡ ሲጭንብን ፡ መዓት ማርከሻው ፡ መዝሙር ፡ ነው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና ጥንትም ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ መች ፡ ይበገርና በክረምት ፡ በበጋ ፡ በህመም ፡ በጤና በክብር ፡ በውርደት ፡ በድል ፡ እንደገና በማግኘት ፡ በማጣት ፡ በትርፍ ፡ በኪሳራ ስንቱን ፡ አቋርጠናል ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ ፀሐይ ፡ ፈነጠቀች ፡ ደረሰ ፡ ጠዋቱ ድምጼም ፡ ያስተጋባ ፡ የገደል ፡ ማሚቱ እግዚአብሔርን ፡ ልጥራ ፡ በውዳሴ ፡ አሃዱ ይነጫነጭ ፡ ጠላት ፡ ያው ፡ እንደልማዱ (፫x) በቃላቶች ፡ ውበት ፡ ጤም ፡ ባለው ፡ ዜማ ተነሱ ፡ እንወድስ ፡ ድምጻችን ፡ ይሰማ ፡ የልባችን ፡ ክብደት ፡ አስጨናቂው ፡ ሁሉ እንደ ፡ እያሪኮ ፡ ግንብ ፡ ይናዳል ፡ ከውሉ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.