Loading
ምህረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እንድሆን ፡ እሻለሁ እኔ ፡ ግን ፡ በቀልን ፡ ወዳጅ ፡ አድርግያለሁ ነፍሴ ፡ ተጎሳቁላ ፡ ፍጹም ፡ ሳያምርባት ተኮንና ፡ እንዳትኖር ፡ ይቅርታን ፡ አስተምራት አዝ፦ ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ አልሆን ፡ እያለው እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ ወንድሜን ፡ ማቁሰሌ ፡ እጅግ ፡ ይረሳኛል የተበደልኩትን ፡ መቁጠር ፡ ይጥመኛል ምን ፡ አለበት ፡ ዛሬ ፡ ልቤን ፡ ብትጠርበው መቀጥቀጫው ፡ ብረት ፡ መዶሻው ፡ በእጅህ ፡ ነው አዝ፦ ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ አልሆን ፡ እያለው እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ እጄን ፡ ለአንተ ፡ ሰጠው ፡ አንተ ፡ እንድታስተምረኝ ለውጠኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይሄው ፡ በፊትህ ፡ ነኝ የበደለኝን ፡ ሰው ፡ ይቅር ፡ ብዬ ፡ እንዳልፈው በቀልን ፡ ሳላስብ ፡ በፍቅር ፡ እንዳቅፈው አዝ፦ ይቅርታን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤ ፡ አልሆን ፡ እያለው እግሬ ፡ የሚራመደው ፡ ሸካራ ፡ መንገድ ፡ ነው የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ድካሜን ፡ ታውቃለህ ዳብሰኝ ፡ እንደገና ፡ ትለውጠኛለህ ምህረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እንድሆን ፡ እሻለሁ እኔ ፡ ግን ፡ በቀልን ፡ ወዳጅ ፡ አድርግያለሁ ነፍሴ ፡ ተጎሳቁላ ፡ ፍጹም ፡ ሳያምርባት ተኮንና ፡ እንዳትኖር ፡ ይቅርታን ፡ አስተምራት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.