Loading
እስኪ ፡ አክብሩልኝ ፡ የለወጠኝን (፪x) አዲስ ፡ ስም ፡ ሰጥቶ ፡ የቀየረኝን (፪x) ከማይጠፋው ፡ ዘር ፡ የወለደኝን (፪x) ለቤቱ ፡ አገልጋይ ፡ ያደረገኝን (፪x) እኔም ፡ ላክብረው ፡ ባለው ፡ ዘመኔ ላዳነኝ ፡ ለርሱ ፡ ለዚህ ፡ መድህኔ ብዘምርለት ፡ ሁሌ ፡ ብናገር አይበዛበትም ፡ ላረገው ፡ ነገር ስንቱን ፡ አውርቼ ፡ የቱን ፡ ልተው ፡ ውለታው ፡ በዝቷል (፪x) የማዳኑን ፡ ክንድ ፡ በእኔ ፡ ለፍጥረት ፡ ገልጧል (፪x) የእኔን ፡ መለወጥ ፡ ያየ ፡ ይበል ፡ አይበቃም (፪x) ገና ፡ እጁ ፡ አላጠረም ፡ ያድናል ፡ ሌላም (፪x) ክሩ ፡ በመርፌ ፡ የገባለት ፡ ሰው (፪x) የዓይኑም ፡ እምባ ፡ ፈሶ ፡ የታበሰው (፪x) በሩጫ ፡ ሜዳ ፡ መስመር ፡ ከያዘ (፪x) ደካማው ፡ ሲወድቅ ፡ ብርቱው ፡ ካገዘ (፪x) በመከናወን ፡ ማን ፡ ቅር ፡ ይሰኛል አእምሮ ፡ ከሌለው ፡ ግን ፡ ቅር ፡ ይለዋል ማሰብ ፡ የሚችል ፡ አእምሮው ፡ ጤነኛ መከናወንን ፡ ይወዳልና ታዲያ ፡ ምነው ፡ ቅር ፡ አላችሁ ፡ ስይዝ ፡ መስመሩን (፪x) መከናወን ፡ ሲሆንልኝ ፡ ሲያወርሰኝ ፡ ክብሩን (፪x) ከዚያ ፡ ካስጨናቂው ፡ አለም ፡ ሳመልጥ ፡ በርሬ (፪x) ተከትሎኝ ፡ መምጣት ፡ እንጂ ፡ አይጠቅምም ፡ ወሬ (፪x) ዕድሜዬን ፡ ሲጨምር ፡ ዓመት ፡ ሲበዛ (፪x) ሲያሸጋግረኝ ፡ መስሎኝ ፡ የዋዛ (፪x) ስቀልድባት ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ (፪x) መቼ ፡ አስቻለው ፡ ሲያየኝ ፡ ከሰማይ (፪x) ለካ ፡ አስቀድሞ ፡ አስቦኝ ፡ ኖሯል የመለወጤ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደርሷል እርሱ ፡ የመደበው ፡ ሰዓቱ ፡ አያልፍ ጌታ ፡ ኢየሱሴን ፡ አግኝቼው ፡ ሳላርፍ እኔም ፡ አላለፍኩ ፡ ከቀኑ ፡ ተማረኩለት (፪x) የርሱ ፡ ፍቅር ፡ አይሎ ፡ እንጂ ፡ ምን ፡ አረግኩለት (፪x) ምን ፡ አይቶብኝ ፡ ነው ፡ እንዳልል ፡ ራሱን ፡ አይቶ ፡ ነው (፪x) ለውጦ ፡ ከቀያየረኝ ፡ ከልካዩስ ፡ ማነው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.