Loading
ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ላማ ፡ ሰበቅታኒ [1][2] ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ማልቀስህ ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ እንዲያ ፡ መዋተትህ ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ መሞትህ ዎይ (፲፫x) ይዘዉህ ፡ ሲሄዱ ፡ እንደሚታረድ ፡ በግ ዝም ፡ ብለህ ፡ እየሄድክ ፡ አንዳች ፡ ሳትሟገት ማነኝ ፡ ለመሆኑ ፡ እንዴት ፡ እወደድከኝ ከክብር ፡ ላይ ፡ ወርደህ ፡ የተዋረድክልኝ አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ አቤቱ ፡ መውደድህ ፡ ስፋቱ አይመረመርም ፡ በሰው ፡ ዘንድ ታላቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መውደድ ፊቴ ፡ ድቅን ፡ ይላል ፡ የእሾህ ፡ ጉንጉኑ የጅራፉ ፡ ብዛት ፡ የገላ ፡ ሰንበሩ ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ፡ ላማ ፡ ሰበቅታኒ [1][2] ብለህ ፡ ስትጨነቅ ፡ ስለእኔ ፡ ስትማቅቅ አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ አቤቱ ፡ መውደድህ ፡ ስፋቱ አይመረመርም ፡ በሰው ፡ ዘንድ ታላቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መውደድ ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ጻድቅ ፡ አይደለህ ፡ ዎይ ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ንጹህ ፡ አይደለህ ፡ ዎይ ጻድቅ ፡ ሰው ፡ በመስቀል ፡ እርቃኑን ፡ አደረ ስለ ፡ ኃጥያተኞች ፡ ደሙን ፡ አፈሰሰ ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ማልቀስህ ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ እንዲያ ፡ መዋተትህ ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ መሞትህ ዎይ (፲፫x) አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ አቤቱ ፡ መውደድህ ፡ ስፋቱ አይመረመርም ፡ በሰው ፡ ዘንድ ታላቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መውደድ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.