Loading
አዝ፦ ከእናቴም ፡ ከአባቴም ፡ ይልቅ ፡ የሚጠጋጋኝ ፡ ዘመዴ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መከታ ፡ ለእኔ ፡ አፍቃሪ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x) ፍቅሩን ፡ ሳስብ ፡ ይደንቀኛል ፡ ለእኔ ፡ ያሳየው ፡ ምህረቱ ባወራው ፡ ባወራው ፡ አያልቅ ፡ ችሎኝ ፡ አለሁ ፡ በቤቱ ትዕግሥቱ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አይሰለችም ፡ ይሸከማል መልካም ፡ የበጐች ፡ እረኛ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ከየት ፡ ይገኛል አዝ፦ ከእናቴም ፡ ከአባቴም ፡ ይልቅ ፡ የሚጠጋጋኝ ፡ ዘመዴ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መከታ ፡ ለእኔ ፡ አፍቃሪ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x) ውድ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታዬ ፡ ዕንቁና ፡ ወርቅን ፡ ያስንቃል ጠረኑ ፡ ከሩቅ ፡ የሚስብ ፡ መዓዛውም ፡ ደስ ፡ ያሰኛል ፍቅር ፡ አለው ፡ ልብ ፡ የሚያረካ ፡ ወዳጄ ፡ ወረት ፡ አያውቅም ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ለውጧል ፡ ፍቅሩን ፡ በሞት ፡ ገልጾልኛል አዝ፦ ከእናቴም ፡ ከአባቴም ፡ ይልቅ ፡ የሚጠጋጋኝ ፡ ዘመዴ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መከታ ፡ ለእኔ ፡ አፍቃሪ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x) ታማኝ ፡ ነው ፡ የማይለወጥ ፡ ጓደኛ ፡ ጊዜ ፡ አይቶ ፡ የማይርቅ የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ዋሴ ፡ ኢየሱስ ፡ አዳኝ ፡ ለነፍሴ ድቅድቅ ፡ ጨለማን ፡ የሚገፍ ፡ ብርሃን ፡ ይሁን ፡ ይብራ ፡ ያለ ድንቁ ፡ የሰላም ፡ አለቃ ፡ ኧረ ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ አለ አዝ፦ ከእናቴም ፡ ከአባቴም ፡ ይልቅ ፡ የሚጠጋጋኝ ፡ ዘመዴ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መከታ ፡ ለእኔ ፡ አፍቃሪ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.