Loading
አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ እየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ እጅ ፡ ሰጥቻለሁ ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ (፪x) ብዙ ፡ የከበሩ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ሞልተው ታላቅ ፡ ነኝ ፡ ባዩን ፡ ልታሳፍረው እኔን ፡ መረጥከኝ ፡ ዓሣ ፡ አጥማጁን ፡ ሰው ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ ፡ ፍቅርህ ሀብታም: ደሀ ፡ አይል ፡ አመራረጥህ ለእኔም ፡ ደረሰኝ ፡ ድንቅ ፡ ማዳንህ አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ እየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ እጅ ፡ ሰጥቻለሁ ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ መች: ያልቃል፡ ጥረቴ ፡ ለዚህ ፡ ሥጋዬ ቀን ፡ ከሌት፡ ስደክም ፡ መረቤን ፡ ጥዬ ምንም ፡ ላላገኝ ፡ በድካም ፡ ዝዬ አንተ ፡ ግን ፡ መጥተህ ፡ ተዓምርን ፡ ሰራህ መላው ፡ ሕይወቴን ፡ መገረም ፡ ሞላ ሥሜን ፡ ተግባሬን ፡ ኑሮዬን ፡ ቀየርክ አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ እየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ እጅ ፡ ሰጥቻለሁ ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ ከኋላዬ ፡ ና ፡ ወድጄሃልሁ ለማዳን ፡ ሥራ ፡ መርጬሃልሁ ሰዎችን ፡ አጥማጅ ፡ አደርግሃልሁ ኣለኝ፡ ጌታዬ ፡ እኔም ፡ ተረታሁ ከልብ ፡ ወደድኩህ ፡ ሕይወቴን ፡ ሰጠሁ እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ አመልክሃለሁ አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ እየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ እጅ ፡ ሰጥቻለሁ ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ የዋህነትህ፡ ትህትናህ ፡ ነው: የሳበኝ በኃይል ፡ በጉልበት ፡ አላስገደድከኝ ድንቅ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው ፡ ያንበረከከኝ ልከተል ፡ ወሰንኩ ፡ ከልብ ፡ ጌታዬ በነገር ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ ታምኜ መረብ ፡ ታንኳዬን ፡ ሁሉንም ፡ ጥዬ አዝ፦ ድንጋዩ ፡ ልቤ ፡ ጠጣሩ ፡ ልቤ መች ፡ በቀላሉ ፡ ታዛዥ ፡ ነበረ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ ውስጤን ፡ ሰበረ ተረትቻለሁ ፡ ተሸንፌያለሁ እየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ እጅ ፡ ሰጥቻለሁ ዛሬ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማርኬያለሁ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.