Loading
አዝ፦ በሠማይ ፡ ዙፋኑ ፡ በመቅደሱ ፡ ያለው የፍጥረት ፡ ፈጣሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው ዓይኑ ፡ እንዳየ ፡ አይፈርድ ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማ በምክሩ ፡ ትክክል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱማ ልብን ፡ ለይቶ ፡ የሚመረምረው እንደሰው ፡ አይደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው የሚያድን ፡ ነው ፡ ደግሞ ፡ የሚራራ አቤቱ ፡ ማረኝ ፡ ላለ ወደ ፡ እርሱ ፡ ለተጠጋ ውድ ፡ ልጁ ፡ በመረቀልን ፡ በር ወደ ፡ እርሱ ፡ መግባት ፡ አለ ፡ አሄ ታላቅ ፡ ስሙ ፡ ይክበር በምክሩ ፡ ጠቢብ ፡ ፍቅሩ ፡ የላቀ በልጆቹ ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ የደመቀ ምሥጋና ፡ ሞላ ፡ በማደሪያው ፡ ላይ በመንጋው ፡ መልካም ፡ ማዳኑን ፡ ሲታይ አዝ፦ በሠማይ ፡ ዙፋኑ ፡ በመቅደሱ ፡ ያለው የፍጥረት ፡ ፈጣሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው ዓይኑ ፡ እንዳየ ፡ አይፈርድ ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማ በምክሩ ፡ ትክክል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱማ ልብን ፡ ለይቶ ፡ የሚመረምረው እንደሰው ፡ አይደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው ታናሹን ፡ ሰው ፡ ለክብር ፡ የሚያበቃው የዳዊት ፡ የሙሴ ፡ አምላክ ፡ አሄ ፡ ለትሁቱ ፡ ጠበቃ የወህኒውን ፡ መዝጊያ ፡ የሚሰብር ለባሪያዎቹ ፡ ፈራጅ ፡ የሚሆን ፡ ሞገስ ፡ ክብር አቢት ፡ እግዚአብሔር ፡ ስራው ፡ ድንቅ ፡ ነው በመልካም ፡ ዜማ ፡ እስቲ ፡ እናምልከው ክብሩ ፡ ይታወጅ ፡ በቤቱ ፡ መድረክ የዘለዓለሙ ፡ አምላክ ፡ ይባረክ አዝ፦ በሠማይ ፡ ዙፋኑ ፡ በመቅደሱ ፡ ያለው የፍጥረት ፡ ፈጣሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው ዓይኑ ፡ እንዳየ ፡ አይፈርድ ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማ በምክሩ ፡ ትክክል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱማ ልብን ፡ ለይቶ ፡ የሚመረምረው እንደሰው ፡ አይደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው ተራሮችን ፡ ከላይ ፡ የሚያጠጣ ለጻድቅ ፡ ለሃጥኡ ፡ አሄ ፡ ፀሐይን ፡ የሚያወጣ ደረቁን ፡ ምድር ፡ የሚያለመልመው ለታናሹ ፡ ሰው ፡ ብርታት ፡ እህ ፡ ሞገስ ፡ የሚሰጠው ምሥጋናን ፡ ያምጡ ፡ ለእርሱ ፡ ያደሩ በመንፈሱ ፡ ኃይል ፡ እየዘመሩ የቤቱ ፡ ካህናት ፡ ምስክሮቹ ስሙን ፡ ያክብሩ ፡ ታማኝ ፡ ባሮቹ አዝ፦ በሠማይ ፡ ዙፋኑ ፡ በመቅደሱ ፡ ያለው የፍጥረት ፡ ፈጣሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው ዓይኑ ፡ እንዳየ ፡ አይፈርድ ፡ ጆሮው ፡ እንደሰማ በምክሩ ፡ ትክክል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እርሱማ ልብን ፡ ለይቶ ፡ የሚመረምረው እንደሰው ፡ አይደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.