Loading
የመዳን ፡ ሚስጢር ፡ ትፈቶልህ ኢየሱስ ፡ ነግቶ ፡ በትላንትህ በፍቅሩ ፡ ስንቴ ፡ ተጽናንተሃል ሁሉን ፡ ትቶ ፡ ከጐንህ ፡ ቆሞልሃል ዛሬ ፡ ምን ፡ ስንፍና ፡ ተበተበህ አጥርተህ ፡ እንዳታይ ፡ ዓይንህን ፡ ከለለህ ከዘላለሙ ፡ ይልቅ ፡ ለሚያልፈው ፡ ተገኘህ ጌታን ፡ በመተውህ ፡ እንደምን ፡ ተሞኘህ አዝ፦ የጌታ ፡ ውድ ፡ ልጅ ፡ የገዛህ ፡ በደሙ ካሰረህ ፡ እስራት ፡ ያድንሃል ፡ ስሙ የተበትበህን ፡ በጣጥሰህ ፡ ተራመድ ከነፍስህ ፡ አብልጠህ ፡ ዓለም ፡ አትውደድ ብርሃንን ፡ ትተህ ፡ ወደ ፡ ጨለመበት ፡ ትገሰግሳለህ የነፍስህን ፡ ሰላም ፡ ከማታገኝበት ፡ ሰፈር ፡ ትሮጣለህ ምንስ ፡ ብትኮበልል ፡ ከኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ወዴት ፡ ትሸሻለህ ለአንተ ፡ ሲል ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ነፍሱን ፡ የሰጠልህ ፡ በመስቀል ፡ የወለ አዝ፦ የአባቴ ፡ ውድ ፡ ልጅ ፡ የገዛህ ፡ በደሙ ካሰረህ ፡ እስራት ፡ ያድንሃል ፡ ስሙ የተበትበህን ፡ በጣጥሰህ ፡ ተራመድ ከነፍስህ ፡ አብልጠህ ፡ ዓለም ፡ አትውደድ የመዳን ፡ ሚስጢር ፡ ትፈቶልህ ኢየሱስ ፡ ነግቶ ፡ በትላንትህ በፍቅሩ ፡ ስንቴ ፡ ተጽናንተሃል ሁሉን ፡ ትቶ ፡ ከጐንህ ፡ ቆሞልሃል ዛሬ ፡ ምን ፡ ስንፍና ፡ ተበተበህ አጥርተህ ፡ እንዳታይ ፡ ዓይንህን ፡ ከለለህ ከዘላለሙ ፡ ይልቅ ፡ ለሚያልፈው ፡ ተገኘህ ጌታን ፡ በመተውህ ፡ እንደምን ፡ ተሞኘህ አዝ፦ የጌታ ፡ ውድ ፡ ልጅ ፡ የገዛህ ፡ በደሙ ካሰረህ ፡ እስራት ፡ ያድንሃል ፡ ስሙ የተበትበህን ፡ በጣጥሰህ ፡ ተራመድ ከነፍስህ ፡ አብልጠህ ፡ ዓለም ፡ አትውደድ እንዴት ፡ ሊሆን ፡ ሰበብ ፡ የአንተ ፡ መገፋት ፡ ቢነሳብህ ፡ ዱላ ይከፍል ፡ የለ ፡ ወይ ፡ ለሁሉ ፡ እንደስራው ፡ ብትታገስ ፡ ኋላ ወንድሜ ፡ ተመለስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ሚበጅህ ፡ ምን ፡ ቢበዛ ፡ ሰልፉ ዛሬም ፡ ይወድሃል ፡ ፍቅሩ ፡ አልቀነሰም ፡ ግባ ፡ ወደ ፡ እቅፉ አዝ፦ የአባቴ ፡ ውድ ፡ ልጅ ፡ የገዛህ ፡ በደሙ ካሰረህ ፡ እስራት ፡ ያድንሃል ፡ ስሙ የተበትበህን ፡ በጣጥሰህ ፡ ተራመድ ከነፍስህ ፡ አብልጠህ ፡ ዓለም ፡ አትውደድ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.