Loading
ለኔ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ያስገርመኛል ለኔ ፡ ያለህ ፡ ምህረት ፡ ያስደንቀኛል ለኔ ፡ ያለህ ፡ ትዕግሥት ፡ ያስገርመኛል ለኔ ፡ ያለህ ፡ ትኩረት ፡ ያስደንቀኛል መተላለፌን ፡ ደምስሰህ ፡ ተቀበልከኝ በመንገዴ ፡ እንድጠፋ ፡ መቼ ፡ ተውከኝ ከፊቴ ፡ ሆነህ ፡ እግሮቼን ፡ የምትመራ ስጋቴን ፡ ሰብረህልኛል ፡ እንዳልፈራ በጎ ፡ ስጦታ ፡ ፍፁም ፡ በረከት ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሆኖልኛል ፡ በምህረት በነፍስህ ፡ የገዛሃት ፡ ይቺ ፡ ነፍሴ ምሥጋናህን ፡ አትረሳም ፡ ሁልጊዜ አዝ፦ ለኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ያስገርመኛል ለኔ ፡ ያለህ ፡ ምህረት ፡ ያስደንቀኛል ለኔ ፡ ያለህ ፡ ትዕግሥት ፡ ያስገርመኛል ለኔ ፡ ያለህ ፡ ትኩረት ፡ ያስደንቀኛል የውስጤን ፡ ነገር ፡ ምነግርህ ፡ የማወጋህ ልቤ ፡ በአንተ ፡ ተማምኖ ፡ ተረጋጋ አሳረፍከኝ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ተመልክተህ ጩኸቴን ፡ የሚሰማ ፡ ማን ፡ እንዳንተ በጎ ፡ ስጦታ ፡ ፍፁም ፡ በረከት ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሆኖልኛል ፡ በምህረት በነፍስህ ፡ የገዛሃት ፡ ይቺ ፡ ነፍሴ ምሥጋናህን ፡ አትረሳም ፡ ሁልጊዜ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.