Loading
እኔማ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ስንቱን ፡ አወራለሁ የቱንስ ፡ አውርቼ ፡ የቱን ፡ እተዋለሁ ያደረገልኝን ፡ ብቆጥር ፡ በየተራ ከአዕምሮዬ ፡ በላይ ፡ ሆነ ፡ የእርሱ ፡ ሥራ እኔማ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ስንቱን ፡ ላውራ ከአዕምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ሥራ (፪x) ክብር ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ክብር ፡ የኢየሱስ ፡ ነው (፪x) ተመስገን ፡ የምለው ፡ ካሳ ፡ ሆኖ ፡ አይደለም የጌታን ፡ ውለታ ፡ የሚክሰው ፡ የለም ክበርም ፡ የምለው ፡ ስለሚገባው ፡ ነው ለውለታው ፡ ምላሽ ፡ ሊሰጥ ፡ የሚችል ፡ ማነው እኔማ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ስንቱን ፡ ላውራ ከአዕምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ሥራ (፪x) አዝ፦ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ/ኢየሱሴ ፡ ወዳጄ ፡ እንከን ፡ የሌለህ ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ ታጠግበኛለህ (፪x) ስለዚህ (፪x) ፡ በፍፁም ፡ ልቤ ፡ ጌታዬ ፡ ወድሃለሁ ዘመኔን (፪x) ፡ እያከበርኩህ ፡ ለመኖር ፡ ወስኛለሁ (፪x) ከእርሱ ፡ የሆነውን ፡ ለእርሱ ፡ አቀርባለሁ እኔማ ፡ ምን ፡ አለኝ ፡ ምን ፡ እሰጠዋለሁ እንዲሁ ፡ በፀጋው ፡ ፊቱ ፡ አቁሞኛል ስለፈቀደልኝ ፡ አመስግን ፡ ብሎኛል ስለፈቀደልኝ ፡ አሃሃ ፡ አመስግን ፡ ብሎኛል ፡ አሃሃ ስለፈቀደልኝ ፡ ኦሆሆ ፡ አክብረኛል ፡ ብሎኛል ፡ አሃሃ አዝ፦ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ/ኢየሱሴ ፡ ወዳጄ ፡ እንከን ፡ የሌለህ ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ ታጠግበኛለህ (፪x) ስለዚህ (፪x) ፡ በፍፁም ፡ ልቤ ፡ ጌታዬ ፡ ወድሃለሁ ዘመኔን (፪x) ፡ እያከበርኩህ ፡ ለመኖር ፡ ወስኛለሁ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.