Loading
የምድረበዳ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ (አሃሃ) ፡ ሁሉን ፡ ያለፍኩብህ የምድረበዳ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ (አሃሃ) ፡ ሁሉን ፡ ያረሳሁብህ ኧረ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x) እኔ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም ኧረ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x) እኔ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x) ዓሣ ፡ ከውኃ ፡ ውጭ ፡ እንደማይኖር ፡ እስትንፋስ ፡ ፡ ርቆት ሕይወቴም ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ የሌለህበት ሸካራው ፡ መንገዴን ፡ አለስልሰህ ፡ በፍቅር ፡ ይዘኸኝ ጥልቅህ ፡ ፍቅርህ ፡ ይዞ ፡ እየመራኝ ፡ በሕይወት ፡ አኖረኝ አስፈሪውን ፡ መንገድ ፡ ሆነህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ በእጆችህ ፡ ይዘኸኝ ፡ እንዴት ፡ ልቤ ፡ ይፍራ (፪x) ሲከፋኝ ፡ ስጨነቅ ፡ አጠገቤ ፡ ነህ ፡ ግራ ፡ ሲገባኝ ከጐኔ ፡ ምትቆም ፡ ሳትሰለቸኝ ፡ ምታበረታኝ የልጅነቴ ፡ አምላክ ፡ ምትሸከመኝ ፡ ከነማንነቴ የሕይወት ፡ ማብቂያ ፡ ነህ ፡ መደምደሚያዬ ፡ የመጨረሻዬ አስከፊውን ፡ መንገድ ፡ ሆነህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ በእጆችህ ፡ ይዘኸኝ ፡ እንዴት ፡ ልቤ ፡ ይፍራ (፪x) የምድረበዳ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ (አሃሃ) ፡ ሁሉን ፡ ያለፍኩብህ የምድረበዳ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ (አሃሃ) ፡ ሁሉን ፡ ያረሳሁብህ ኧረ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x) እኔ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም ኧረ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x) እኔ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.