Loading
አዝ፦ ይሁን ፡ ሆይ (፪x) ፈቃድህን ፡ ልጠይቅ ፡ ይሁን ፡ ሆይ የእኔ ፡ መንገድ ፡ የሚያምረው አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ስትመራኝ ፡ ነው (፪x) አንተ ፡ የሌለህበት ፡ ብራብ ፡ ላያጠግበኝ መንገዴም ፡ ላይቀና ፡ ሕይወት ፡ ላይሆንልኝ ልጠይቅ ፡ ፈቃድህን ፡ አባቴ ፡ ነህና እሾህ ፡ ማይኖረው ፡ መንገዴ ፡ ሲቀና (፪x) አሃሃ ፡ በጐ ፡ መስሎኝ ፤ አሃሃ ፡ በዓይኔ ፡ አይቼ አሃሃ ፡ ተጐዳሁኝ ፤ አሃሃ ፡ ውስጥ ፡ ገብቼ አሃሃ ፡ ያየህልኝን ፤ አሃሃ ፡ እንድወርሰው አሃሃ ፡ ምራኝ ፡ ጌታ ፤ አሃሃ ፡ እንድደርሰው (፪x) አዝ፦ ይሁን ፡ ሆይ (፪x) ፈቃድህን ፡ ልጠይቅ ፡ ይሁን ፡ ሆይ የእኔ ፡ መንገድ ፡ የሚያምረው አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ስትመራኝ ፡ ነው (፪x) በሕይወቴ ፡ ስጓዝ ፡ ባለፉት ፡ ዘመናት ራሴን ፡ ሰምቼ ፡ ወጣሁኝ ፡ ለጥፋት ያኔ ፡ ይበቃኛል ፡ የሳትኩት ፡ መንገዴ ምራኝ ፡ እንደቃልህ ፡ በአንተ ፡ ይሁን ፡ ውዴ (፪x) አሃሃ ፡ በጐ ፡ መስሎኝ ፤ አሃሃ ፡ በዓይኔ ፡ አይቼ አሃሃ ፡ ተጐዳሁኝ ፤ አሃሃ ፡ ውስጥ ፡ ገብቼ አሃሃ ፡ ያየህልኝን ፤ አሃሃ ፡ እንድወርሰው አሃሃ ፡ ምራኝ ፡ ጌታ ፤ አሃሃ ፡ እንድደርሰው (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ መንገድ ፡ የሚያምረው አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ጌታዬ ፡ ስትመራኝ ፡ ነው ይሁን ፡ ሆይ (፪x) ፈቃድህን ፡ ልጠይቅ ፡ ይሁን ፡ ሆይ የእኔ ፡ መንገድ ፡ የሚያምረው አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ስትመራኝ ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.