Loading
ነፍሴም ፡ እንደ ፡ ውኃ ፡ አንተን ፡ ተጠማች በቀንም ፡ በማታም ፡ እየናፈቀች (፪x) ያሰብኩት ፡ ተሳክቶ ፡ እርካታ ፡ ሳይኖረኝ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ሲመጣ ፡ ህይወት ፡ ፈለቀልኝ (፪x) እኔማ ፡ አላይ ፡ ወደሌላ የልቤ ፡ ሚገባው ፡ ሌላ ፡ የለምና ኑሮዬም ፡ ቢሞላ ፡ ሚመች እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆነ ፡ እንጂ ደመና ፡ አልባ ፡ ሰማይ ፡ ተንጣሎ ፡ ከፊቴ ወጀብ ፡ ሲያፏጭባት ፡ ተፋልሳ ፡ ሕይወቴ በማይቋጭ ፡ ዙሪት ፡ ተስፋ ፡ አጥቼ ፡ ሳለሁ የዘላለም ፡ ተስፋ ፡ ኢየሱስን ፡ አገኘው (፪x) እኔማ ፡ አላይ ፡ ወደሌላ ፡ እርካታ ፡ ሚሞላ ፡ ሌላ ፡ የለምና ኑሮዬም ፡ ቢሞላ ፡ ሚመች እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆነ ፡ እንጂ በልቶም ፡ ይርበዋል ፡ አግኘቶ ፡ ይጐለዋል ዛሬ ፡ አገኘሁኝ ፡ ሲል ፡ ኪሳራ ፡ ይቀድመዋል ከምንጩ ፡ የሸሸ ፡ ነፍስ ፡ ከአንተ ፡ ርቆ ፡ የሄደ የወጣ ፡ ሲመስለው ፡ ወደታች ፡ ወረደ (፪x) እኔማ ፡ አላይ ፡ ወደሌላ እርካታ ፡ ሚሞላ ፡ ሌላ ፡ የለምና ኑሮዬም ፡ ቢሞላ ፡ ሚመች እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆነ ፡ እንጂ እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እርካታዬ (፰x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.