Loading
ከህልውናህ ሰፈር ከምትገኝበት ንግግር ፀሎቴ አንተው ከሆንክበት ጠንቀቅ ካላልኩኝ ካልጠበቅሁ እግሮቼን እልፍ የሚለይ ጉዳይ ከቦኛል ዙሪያዬን በገለባ ናፍቆት በጠፊ ፍለጋ አይለፍብኝ ቀኔ አርቆኝ ካንተ ጋር ወደተራራው ጫፍ ሳበኝ ወደራስህ ነፍሴም ድና እንድትቀር አቅልጣት በክብርህ በገለባ ናፍቆት በጠፊ ፍለጋ አይለቅብኝ ቀኔ አርቆኝ ካንተ ጋር ወደተራራው ጫፍ ሳበኝ ወደራስህ ነፍሴም ድና እንድትቀር አቅልጣት በክብርህ መባዘን አይደለም መዋል ካንተ ጋራ ስለ ላዩ ምክርህ ነፍሴን ስታዋራ ሰብሰብ ብሏል ቀኔ አልተዝረከረከም የማይወሰድ እድል ከዚህ በላይ የለም አንተን ብቻ ይሁን የማይበት ዓይኔ ልቤም ሄዶ ይቅር ከላዩ ሰፈሬ ጆሮዬም ይቀስር ከላይኛው ሃገር አጥፋኝ ከምድሩ ፍለጋዬ ይሰወር አንገቴን አስግጌ በመናፈቅ ህይወት ለአፍታ ጎንበስ ሳልል አንዳች ከሌለበት እጅ ሰጥቶ ላንተ ውስጥና ውጪዬ ስንቄ ሆኖ ፍቅርህ ይጠቅለል እድሜዬ ጥሜ ረሃቤ ናፍቆቴ መሻቴ ጉጉቴ ፍላጎቴ ሩጫዬ መገስገሴ አንተን ለማግኘት ነው በቃ ፈልግሃለሁ በቃ ተርቤሃለሁ በቃ እጅግ ጠምተኸኛል በቃ አይኖቼ ናፍቀውሃል በቃ ናፍቄሃለሁ በቃ ደጅ ደጅ አያለሁ በቃ የውስጤ ጥም ነህ በምንም የማለውጥህ አንተን የተራበ ሚጠግበው አንተን ነው አንተን የተጠማ ሚረካው አንተን ነው ፊትህን የፈለገ ሲያገኝህ ያርፋል ፈልጎ ክብርህን መቼ በጅህ ይረካል አይደለሁም ሰነፍ ተመከርኩ በቃልህ የውስጤን እረሃብ አይደፍነውም የእጅህ ነፍሴን የምታረካ ሙላት ነህ የልቤ የኑሮዬ ፍሰሃ የዕድሜ ልክ ሃሳቤ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.