Loading
ሥምህን ፡ አውቅኩት ፡ ተረዳሁት ፡ ደግሞም ፡ ታምኜበታለሁ የፀና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ከስንቱ ፡ አምልጬ ፡ ተጠግቼው ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ደጅህን ፡ ጠናሁት ፡ አንኳኳሁት ፡ ከፍተህልኝ ፡ ተቀብለኸኛል በፍቅር ፡ እጆችህ ፡ እቅፍ ፡ አርገህ ፡ ወደ ፡ ራስህ ፡ አስጠግተኸኛል (፪x) አቤት ፡ ያለው ፡ ሰላም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሲጠጋጉ ፡ ወደ ፡ ደረትህ ማዳመጥ ፡ ስትናገር ፡ የፍቅርን ፡ ቋንቋ መቼ ፡ ይታወቃል ፡ ወፎቹ ፡ ሲንጫጬ ፡ ለሊቱም ፡ ሲነጋ (፪x) ኃያል ፡ ሆይ ፡ በኃይልህ ፡ ኃያል ፡ አደረግከኝ ብርቱ ፡ ሆይ ፡ በብርታትህ ፡ ብርቱውን ፡ አደረግከኝu እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ ፡ እየማርክኝ (፪x) በልዑሉ ፡ አምላክ ፡ መጠጊያ ፡ መኖሬ ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ማደሬ ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ በላባዎቹ ፡ ጋርዶኝ ከጠላት ፡ ፍላፃ ፡ አንዱም ፡ አላገኘኝ ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል በአጠገቤ ፡ ሺህ ፡ በቀኜም ፡ አስር ፡ ሺህ እየበተነልኝ ፡ ሆኛለሁ ፡ ድል ፡ ነሺ ይሄ ፡ ካላስመካኝ ፡ የቱ ፡ ያስመካኛል መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ከእልፍ ፡ አስጥሎኛል አስጥሎኛል ፡ እንዲህ ፡ አድርጎ ከአንደበቴ ፡ ምስጋናን ፡ ወዶ (፰x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.