Loading
ይሆንልኛል ፡ ይሳካልኛል ሥጋት ፡ ሰፈሬን ፡ ከራቀ ፡ ሰንበትበት ፡ ብሏል (፬x) አልረሳውም ፡ ማንነቴን በደም ፡ ዋጋ ፡ መገዛቴን ንጉሥ ፡ ከላይ ፡ ሆኖ ፡ እንዳየኝ ልጄ ፡ ምርጤ ፡ ርስቴ ፡ እንዳለኝ (፪x) በምሰማው ፡ ሌላ ፡ ውሸት አልጥለውም ፡ ይህን ፡ ዕውነት ንጉሥ ፡ ልጁን ፡ የላከልኝ የተወደድኩ ፡ ምርጥ ፡ ዘር ፡ ነኝ (፪x) አይሆንም ፡ አይሰምርም ፡ ያለው ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ነው? ሁኔታ ፡ ነው? ነቅቻለሁ! ቃሉን ፡ በንጉሥ ፡ ቃል ፡ ሽራለሁ ተደርጐልኛል ፡ ተሳክቶልኛል ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ አይሆንም ፡ አይሰምርም ፡ ያለው ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ነው? ጠላቴ ፡ ነው? ነቅቻለሁ! ቃሉን ፡ በንጉሥ ፡ ቃል ፡ ሽራለሁ ይሆንልኛል ፡ ይሳካልኛል ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ ቁም ፡ ነገር ፡ አድርጐት ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ ክብሩን ፡ ሁሉ ፡ ትቶ ፡ ወርዷል ፡ ከላይ አቅሜን ፡ አውቃለሁ ፡ በእርሱ ፡ ያለኝን የሆንኩትን ፡ ሆኖ ፡ ያረገኝን (፪x) ደዌ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ላይሰለጥን፡ እርግማን ፡ በቤቴ ፡ እንዳይገኝ ዝቅታ ፡ ላይሆንብኝ ፡ በላዬ፡ መሸነፍ ፡ መረታት ፡ ላያገኘኝ ከፍ ፡ ላለ ፡ ሕይወት ፡ በክርስቶስ ፡ ታጭቻለሁ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ዕጣ ፡ ፈንታዬ የሆንኩትን ፡ ሁሉ ፡ ሆኖልኛል ፡ በድል ፡ ተፈጽሟል ፡ ጐዳናዬ ያለቀ ፡ ነው ፡ ያኔ ፡ ድሮ የእኔ ፡ ጉዳይ ፡ የእኔ ፡ ኑሮ በቀራኒዮ ፡ ተራራ ፡ ላይ ተፈጽሟል ፡ ብሎኛል ፡ የእኔ ፡ ጉዳይ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.