Loading
እንደ ፡ ሲና ፡ ምድር ፡ እንደ ፡ በረሃዉ ጠል ፡ ከእርሱ ፡ እርቆ ፡ . (1) . ትካዜ ፡ ሰፍኖበት ፡ ሆኖ ፡ ረዳት ፡ አልባ እንዲህ ፡ ያለው ፡ ምስኪን ፡ ልምላሜን ፡ ሰማ አሄ ፡ ልምላሜን ፡ ሰማ አዝ፦ ምን ፡ እልሃለው (፫x) ከእግርህ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ፡ አመሰግናለው (፪x) ብቸኝነት ፡ ዓለም ፡ ወግ ፡ ሆኖ ፡ በሕይወቴ አጠገቤ ፡ ነበር ፡ ለካስ ፡ ደጉ ፡ አባቴ ቅርበቱን ፡ አወኩት ፡ ድምጹንም ፡ ሰማሁት እንደ ፡ ብዙ ፡ ወዳጅ ፡ ሆኖ ፡ አገኘሁት አሄ ፡ ሆኖ ፡ አገኘሁት ያንን ፡ የጭንቅ ፡ ቀን ፡ የብቸኝነቴን ክንድህ ፡ ባይረዳኝ ፡ ፀጋህ ፡ ባያግዘኝ ኧረ ፡ እኔስ ፡ የት ፡ ነበርኩኝ (፪x) እናት ፡ አባት ፡ ዘመድ ፡ ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ነው ቀን ፡ ከሌት ፡ ስራመድ ፡ ልቤ ፡ የሚያስበው በኛ ፡ ክፉ ፡ ቀናት ፡ ረዳት ፡ በሌላቸው መጽናናት ፡ ሆነልኝ ፡ ዳስሼው ፡ ነክቼው አሄ ፡ ዳስሼው ፡ ነክቼው አዝ፦ ምን ፡ እልሃለው (፫x) ከእግርህ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ፡ አመሰግናለው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.