Loading
አንተ ፡ እኮ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ፡ ነህ አንተ ፡ እኮ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ አንተ ፡ እኮ ፡ ለእኔ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ ሥሜን ፡ በሰማዩ ፡ መዝገብ ፡ መቀመጫዬን ፡ በአብ ፡ ቀኝ እረፍትን ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘመኔም ፡ ቁጥር ፡ የለም ስሄድ ፡ በመላዕክት ፡ ታጅቤ ፡ እኔም ፡ በአምላኬ ፡ ታስቤ ሰማያት ፡ ደስ ፡ እያላቸው ፡ እኔ ፡ መዳኔ ፡ ገርሟቸው በትውልድ ፡ ላላገኘሁት በትምህርት ፡ በዕውቀት ፡ በችሎታ የማያልፍ ፡ ክብር ፡ አውራሼ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ልዩ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነህ ልዩ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ልዩ ፡ ነህ ስለጥበቃህ ፡ አልሰጋም ፡ ተጠብቄ ፡ አይቻለሁ ስለማዳንህ ፡ ብናገር ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ አወራለሁ አባትነትህማ ፡ ለእኔ ፡ ሆኖኝ ፡ ጧት ፡ ማታ ፡ ትዝታ እኖራለሁ ፡ ተደስቼ ፡ በአንተ ፡ በአስደናቂ ፡ ጌታ በዘመድ ፡ አልታመንም ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ በሚጠወልግ ብሩንም ፡ አይቼዋለሁ እንደ ፡ ጉድፍ ፡ ቆጥሬዋለሁ በምንም ፡ የማይገመት ፡ ሀብቴ ትምክህቴ ፡ ልዩ ፡ ኩራቴ የሕይወት ፡ ዘመን ፡ ምርጫዬ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔስ ፡ ጌታዬ ማንም ፡ ላይገዛኝ ፡ ኖራለሁ ፡ ሁሉን ፡ በአንተ ፡ አሸንፌአለሁ የሚገዛኝ ፡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ማንም ፡ የለም ገንዘብ ፡ ሀብት ፡ ዕውቀት ፡ ንብረት ፡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ መጠመድ አበቃ ፡ አከተመለት ፡ ከአንተ ፡ የተገናኘን ፡ ዕለት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.