Loading
እስኪ ፡ ስሙኝ ፡ አንዴ ፡ ስሙኝ ፡ ልንገራችሁ ምስኪኑን ፡ ሲያከብር ፡ በዓይናችሁ ፡ ያያችሁ ኧረ ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ምንስ ፡ ይነገራል አምላክ ፡ ሥራው ፡ ብዙ ፡ ይህንን ፡ አድርጓል (፪x) እስኪ ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ አለ (፫x) እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፫x) ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነው እርሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነው በእርግጥ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነው ልዩ ፡ ነው ፡ እኩያ ፡ የለው እንደ ፡ አባትም ፡ ሆኖ ፡ ከአባትም ፡ በላይ ብዙ ፡ አድርጐልኛል ፡ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ እንዴት ፡ እችላለሁ ፡ በቃላት ፡ ዘርዝሬ ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ ይኸው ፡ በዝማሬ አዝ፦ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው ልባርከው ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x) ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ ፡ በርሱ ፡ ተማምኜ እጅግ ፡ በሚመቸው ፡ ትከሻው ፡ ላይ ፡ ሆኜ እኔ ፡ አልጨነቅም ፡ ምድር ፡ ቢነዋወጥ የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ፈፅሞ ፡ አይለዋወጥ አዝ፦ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው ልባርከው ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x) ወጀቡ ፡ ቢነሳ ፡ ከቶ ፡ አያሰጥመኝም ከኢየሱሴ ፡ ፍቅር ፡ ምንም ፡ አይለየኝም የተናገረኝን ፡ እንደሚፈፅመው ሁልጊዜ ፡ አምነዋለሁ ፡ አምላኬ ፡ ታማኝ ፡ ነው አዝ፦ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው ልባርከው ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x) የእግዚአብሔርን ፡ ክንድ ፡ ማን ፡ ይከለክላል በብርታትስ ፡ በልጦት ፡ ማንስ ፡ ያቆመዋል ሁሉን ፡ እየረታ ፡ ሲሰራ ፡ የኖረው እንደ ፡ ትላንትናው ፡ ዛሬም ፡ ጌታ ፡ ያው ፡ ነው አዝ፦ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው ልባርከው ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x) እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፫x) እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ ማን ፡ አለ (፫x) ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ ነህ አንተስ ፡ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ ነህ ልዩ ፡ ነህ ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.