Loading
አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመሥገን (፰x) ዛሬም ፡ ተመስገን ፡ ነገም ፡ ተመሥገን ሁሌም ፡ ተመሥገን (፪x) ባህሩን ፡ በኃይል ፡ ከፈልከው (ተመሥገን) ሕዝብህን ፡ በድል ፡ መራኸው (ተመሥገን) ጠላት ፡ ጉልበቱ ፡ ተመትቶ (ተመሥገን) አይተናል ፡ ከባሕር ፡ ሰጥሞ አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመሥገን (፰x) ዛሬም ፡ ተመስገን ፡ ነገም ፡ ተመሥገን ሁሌም ፡ ተመሥገን (፪x) ሃያ ፡ አራት ፡ ሽማግሌዎች ፡ ወድቀው ፡ ክብር ፡ ይሰጡሃል መላእክት ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ይገባል ፡ ለአንተ ፡ ይሉሃል እኔም ፡ ባለችኝ ፡ ጊዜ ፡ ላክብርህ ፡ ውዱ ፡ ጌታዬ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ እላለሁ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ገና (፬x) ገና ፡ ገና ፡ መቼ ፡ ይበቃውና ገና ፡ ገና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና ገና ፡ ገና ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና (፪x) አልጠግብ ፡ ባመሰግነው ፡ ተመሥገን ፡ ተመስገን ፡ ብለው ኢየሱሴ ፡ ለኔ ፡ ያረገው ፡ ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው አልውልም ፡ ሳላነሳሳው ፡ ሥሙ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው እንደገና ፡ አከብረዋለሁ ፡ ምሥጋናዬ ፡ እስኪ ፡ ይድረሰው ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ገና (፬x) ገና ፡ ገና ፡ መቼ ፡ ይበቃውና ገና ፡ ገና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና ገና ፡ ገና ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና (፪x) ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ገና (፬x) ገና ፡ ገና ፡ መቼ ፡ ይበቃውና ገና ፡ ገና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና ገና ፡ ገና ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.