Loading
ከሰማያት ፡ በላይ ፡ ያለኸው እረድኤታችን ፡ የሆንከው ከደመናት ፡ በላይ ፡ ተራምደሃል እግዚአብሔር ፡ ማንስ ፡ ይመስልሃል (፪x) ማነው ፡ ሰማይን ፡ የሰራ ማነው ፡ ምድርን ፡ ያፀና ሌላው ፡ ካንተ ፡ በቀር ፡ የለም ጌታ ፡ ነህ ፡ ክበር ፡ ለዘላለም (፪x) ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘላለም ጌታ ፡ ንገስ ፡ ለዘላለም ይነሳና ፡ እስኪ ፡ ይናገር አምላክ ፡ ማነው ፡ ከአንተስ ፡ በቀር በጉልበትህ ፡ ጽናት ፡ ተራምደህ ትኖራለህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ከብረህ (፪x) ታላቅነትህ ፡ ቢወራ ፡ ቢነገር ምንም ፡ አይገልጽህ ፡ ከመደነቅ ፡ በቀር (፪x) እንዲያው ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ባለኝ ፡ አቅም ብዬ ፡ ልለፈው ፡ እንዳተ ፡ የለም (፪x) (እስኪ ፡ ማነው) ማነው ፡ ሰማይን ፡ የሰራ (የሰራ) ማነው ፡ ምድርን ፡ ያቀና (ያጸና) ሌላው ፡ ካንተ ፡ በቀር ፡ የለም (የለም ፡ የለም) ጌታ ፡ ነህ ፡ ግዛን ፡ ለዘላለም (ለዘላለም) (፪x) ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘላለም ጌታ ፡ ንገስ ፡ ለዘላለም (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.