Loading
ስለ ፡ ጻድቅ ፡ ሰው ፡ የሚሞት ፡ መቼም ፡ ቅርብ ፡ ይገኝ እንዴት ፡ ተገኘ ፡ ብዬ ፡ አያስደንቀኝ ስለ ፡ ቸር ፡ ሰው ፡ ቢሆን ፡ እንደዚሁ ፡ ነኝ ፡ እኔ ጊዜዬን ፡ በዚህ ፡ አልፈጅም ፡ ለምኔ ፡ ለምኔ አንድ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ እኔን ፡ ያስደነቀኝ ደካማ ፡ እያለሁ ፡ ሳላውቀዉ ፡ ያወቀኝ ሃጥያት ፡ ያራቀኝ ፡ ከመንገድ ፡ አውጥቶ ኢየሱስ ፡ መለሰኝ ፡ ሞቴን ፡ ሁሉ ፡ ሞቶ ፡ አሃ አዝ፦ እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ንፍስን ፡ የሚያሰጠው እንዴት ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያስወደው (፪x) በአንዷ ፡ አለመታዘዝ ፡ ብዙዎች ፡ ኃጥያተኛ ፡ ሆኑ [1] ከዲያብሎስ ፡ ጋራ ፡ ገሃነም ፡ ሊጣሉ በኢየሱስ ፡ መታዘዝ ፡ ከፍርድ ፡ አምልጠናል [2] የመንግሥተ ፡ ሠማይ ፡ ወራሽ ፡ አድርጐናል አዝ፦ እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ንፍስን ፡ የሚያሰጠው እንዴት ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያስወደው (፪x) ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ያለው ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ ይበልጣል ለእኔ ፡ ባረገው ፡ ነገር ፡ ልቤ ፡ ተሸንፏል የፍቅርንም ፡ ሚስጥር ፡ ያወኩት ፡ በእርሱ ፡ ነው አቀብት ፡ ዳገቱን ፡ የወጣዉ ፡ ለእኔ ፡ ነው በደሙ ፡ ተድቄ ፡ ከቁጣ ፡ ድኛለሁ ጠላትነት ፡ ቀርቶ ፡ ወገን ፡ ተብያለሁ ሰላሙን ፡ ሰብኮኛል ፡ የሰላም ፡ አለቃ የጭንቀቱ ፡ ዘመን ፡ ከእኔ ፡ ላይ ፡ አበቃ ፡ አሃ አዝ፦ (እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው) እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ንፍስን ፡ የሚያሰጠው እንዴት ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያስወደው (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.