Loading
መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አባቴ (፪x) ታስብልኝ ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ አንተም ፡ ልጄን ፡ ብለህ ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x) ይሁንልኝ ፡ ብዬ ፡ የተሟገትኳቸው ባለፈው ፡ ዘመኔ ፡ ኧረ ፡ ብዙ ፡ ናቸው ጊዜ ፡ ፈጀሁ ፡ እንጂ ፡ ከወዲህ ፡ ከወዲያ ምን ፡ ጥልቅ ፡ አስብሎኝ ፡ ደርሶ ፡ በአንተ ፡ ሞያ ትክክል ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ በሥራህ ፡ ጻድቅ ፡ ነህ አንተ ፡ አትታረምም ፡ እንዲህ ፡ አድርግ ፡ ተብለህ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አባቴ (፪x) ታስብልኝ ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ አንተም ፡ ልጄን ፡ ብለህ ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x) እንደው ፡ መጨነቄ ፡ ሁሉ ፡ ከልኩ ፡ አያልፍ አንዳችም ፡ ላልጨምር ፡ አንዳችም ፡ ላላተርፍ ባይገቡኝም ፡ እንኳን ፡ መንገዶቼ ፡ ሁሉ ለአንተ ፡ ግን ፡ አባቴ ፡ ጠርተው ፡ ይታያሉ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ መልካም ፡ ከሆነልኝ እንዳረከኝ ፡ ልሁን ፡ የእኔስ ፡ ይቅርብኝ እኔ ፡ ያልኩት ፡ አልሆነም ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ አልቀረም አሁንም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ ፈቃድህ ፡ ያግኘኝ ስኖር ፡ በዚች ፡ ዓለም አሁንም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ ፈቃድህ ፡ ያግኘኝ ስኖር ፡ በዚች ፡ ዓለም (፪x) እግሮቼን ፡ ከወጥመድ ፡ ማነው ፡ ያወጣቸው ዓይኖቼ ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ናቸው በመረጥከው ፡ መንገድ ፡ አስተምረኸኛል ለማያልፈው ፡ ሕይወት ፡ መኖር ፡ ይሻለኛል ለማያልፈው ፡ መብል ፡ መስራት ፡ ይሻለኛል መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አባቴ (፪x) ታስብልኝ ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ አንተም ፡ ልጄን ፡ ብለህ ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x) እኔ ፡ ያልኩት ፡ አልሆነም ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ አልቀረም አሁንም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ ፈቃድህ ፡ ያግኘኝ ስኖር ፡ በዚች ፡ ዓለም አሁንም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ ፈቃድህ ፡ ያግኘኝ ስኖር ፡ በዚች ፡ ዓለም (፪x) ትክክል ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ በሥራህ ፡ ጻድቅ ፡ ነህ አንተ ፡ አትታረምም ፡ እንዲህ ፡ አድርግ ፡ ተብለህ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.