Loading
እንኳን ፡ ልመካ ፡ እንዲህ ፡ ነኝ ፡ ብዬ እኔ ፡ እኔ ፡ ልል ፡ ቃል ፡ አስረዝሜ 'እ'ን ፡ አስጀምሮ ፡ 'ኔ'ን ፡ የሚያስጨርሰኝ ከራሴ ፡ ምለው ፡ አንዳችም ፡ የለኝ አሁን ፡ የሆንኩትን ፡ መሆን ፡ የመቻሌ ጌታ ፡ በአንተ ፡ እኮነው ፡ አይደለም ፡ በእኔ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተይሁን x ፬ እኔ ፡ ለማለት ፡ "ፓ!" እንዲሉልኝ ፡ ፡ ሰዎች ፡ ብጠራ ፡ ማንም ፡ አይገኝ ፡ በአሸዋ ፡ ላይ ፡ ቤቴን ፡ ስሠራ እርሱ ፡ ነው ፡ ስል ፡ ግን ፡ ተሰብሰቡና ፡ "አዎ" ፡ በሉልኝ ይህን ፡ ላረገው ፡ ታማኙ ፡ ጌታ ፡ (ክብር ፡ አምጡልኝ) ፡ x ፰ ስሙኝ ፡ ወገኖች ፡ ይህን ፡ ስናገር ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፡ ለሆነው ፡ ነገር እንኳን ፡ ልታበይ ፡ እኔን ፡ ላበዛ ፡ ትንፋሽ ፡ መንገዱን ፡ ከፍሎ ፡ እንደገዛ ከቶ ፡ አልመካም ፡ እንዲያው ፡ በከንቱ ፡ ከእኔ ፡ ሳይሆን ፡ ሁሉ ፡ ነው በእርሱ 'እ' ፡ የሚለውን ፡ ፊደል ፡ ጀምሬ ፡ 'ኔ'ን ፡ ለመጨረስ ፡ ኃይል ፡ የለኝ ፡ እኔ እያልኩኝ ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ጌታ ሁሉን ፡ አድርገህ ፡ የምታስመካኝ ፡ ሆንከኝ ፡ አለኝታ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተይሁን x ፬ ኧረ ፡ ምንድነው ፡ ከእኔ ፡ ነው ፡ የምለው ኃይሌ ፡ ብርታቴ ፡ እጄ ፡ ያረገው ማበዛላቸው ፡ ብዙ ፡ እኔዎች ሆኑ ፡ ምላቸው ፡ በእኔ ፡ ክንዶች ምንም ፡ የለኝም ፡ የሚያስብለኝ ፡ እኔ ክብር ፡ ሚገባው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ እንኳን ፡ ልመካ ፡ እንዲህ ፡ ነኝ ፡ ብዬ እኔ ፡ እኔ ፡ ልል ፡ ቃል ፡ አስረዝሜ 'እ'ን ፡ አስጀምሮ ፡ 'ኔ'ን ሚያስጨርሰኝ ከራሴ ፡ ምለው ፡ አንዳችም ፡ የለም ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተይሁን # ፬
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.