Loading
በግብፅ ፡ የነበረውን ፡ የህዝቡን ፡ ጩኸት ፡ የሰማ ፡ ጌታ ጊዜና ፡ ዘመን ፡ ጠብቆ ፡ ወደኔ ፡ መጣ በቃ ፡ አለው (፪x) ፡ ያን ፡ ክፉ በቃ ፡ አለው ፡ ያን ፡ ክፉ ጌታዬ ፡ ከልሎኝ ፡ በክንፉ (፬x) ያቤቱታ ፡ ድምፄ ፡ ወደ ፡ ጆሮው ፡ ደርሶ የምህረት ፡ ፊቱን ፡ ወደኔ ፡ መልሶ ከጨቋኙ ፡ ገዢ ፡ ነፍሴን ፡ አላቋታል ውስጤን ፡ በደስታ ፡ እንዲህ ፡ አስብሎታል ፡ አሄ አስባለሁ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፪x) እላለሁ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፪x) በውርደቴ ፡ መንደር ፡ ክብር ፡ ያየሁበት የቆሰለው ፡ ልቤ ፡ የተፈወሰበት (፪x) እላለሁ ፡ እላለሁ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ የለም ፡ አሜን (፪x) እንደ ፡ ወትሮው ፡ ሰላም ፡ አውለኝ ፡ ብዬ ፡ ስነሳ የፈሮኦንን ፡ ጡብ ፡ ልሰራለት ፡ ከቤት ፡ ስወጣ ያስገባሪዬን ፡ ገመድ ፡ ከላዬ ፡ ሊፈታልኝ አምላኬ ፡ መጣ ፡ ያዘንኩበትን ፡ ቀን ፡ ቀጥሮልኝ ግብፅን ፡ ለቅቄ ፡ ያን ፡ ቀን ፡ ስወጣ ፈርኦን ፡ ሲያየኝ ፡ እንዲህ ፡ አልኩታ ጉልበቴ (፪x) ላዳነኝ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ አትበላው ፡ ከሳሼ በግብፅ ፡ የነበረውን ፡ የህዝቡን ፡ ጩኸት ፡ የሰማ ፡ ጌታ ጊዜና ፡ ዘመን ፡ ጠብቆ ፡ ወደኔ ፡ መጣ በቃ ፡ አለው (፪x) ፡ ያን ፡ ክፉ በቃ ፡ አለው ፡ ያን ፡ ክፉ ጌታዬ ፡ ከልሎኝ ፡ በክንፉ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.