Loading
አዲስ ፡ ሰማይ ፡ አዲስ ፡ ምድር የብርሃን ፡ ሀገር ፡ የብርሃን ፡ ቅጥር ምርአፍ ፡ ተዘግቶ ፡ ምርአፍ ፡ ሲጀመር አየዋለው ፡ ያኔ ፡ በድል ፡ በክብር ሲያልፍ ፡ ፊተኛው ፡ ሰማይ ደግሞ ፡ አንደገና ፡ አዲስ ፡ ሰማይ ሲያበቃ ፡ ይሄኛው ፡ ምድር ዘለዓለም ፡ አለ ፡ የክብር ፡ ምድር (፪x) ጨለማ ፡ ዳግም ፡ በማይሰፍነበት ፀሐይም ፡ ጨረቃም ፡ በሌሉበት በጉ ፡ ብርሃን ፡ ነዉ ፡ ያበራል ሀገር ፡ በክርስቶስ ፡ ይደምቃል አዝ፦ ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋዬ የዘላለም ፡መኖርያዬ ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ የክብር ፡ ተስፋዬ ፡ ከአየሱስ ፡ ጋር ፡ ለዘላለም ፡ መንገሻዬ አይን ፡ ያላየው ፡ ጆሮም ፡ ያልሰማው ጌታ ፡ ለሚወዱት ፡ ያዘጋጀው ልብሳቸውን ፡ በበጉ ፡ ደም ፡ ላጠቡ የሰፋውን ፡ መንገድ ፡ ጥለው ፡ ለዘለቁ አዝ፦ ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋዬ የዘላለም ፡መኖርያዬ ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ የክብር ፡ ተስፋዬ ፡ ከአየሱስ ፡ ጋር ፡ ለዘላለም ፡ መንገሻዬ በተስፋ ፡ ድንበር ፡ በፍቅር ፡ ሀገር የእምነት ፡ ፅናት ፡ ምላሽ ፡ ሲሰምር ሲበሰር ፡ የዘለዓለሙ ፡ ደስታ የታመኑት ፡ የናፈቁት ፡ ላይም ፡ ሲበቃ አዝ፦ ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋዬ ከአየሱስ ፡ ጋር ፡ ለዘላለም ፡ መኖርያዬ ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋዬ ፡ ከአየሱስ ፡ ጋር ፡ ለዘላለም ፡ መንገሻዬ ሌት ፡ በማያውቀው ፡ የቀን ፡ ጅረት ብርሃን ፡ ውሎ ፡ ብርሃን ፡ ማደር ምናለ ፡ ደስታ ፡ ምናለ ፡ ውበት ከክርስቶስ ፡ ጋር ፡ ነግሶ ፡ አንደማየት ሞት ፡ በማይገጥመው ፡ የህይወት ፡ ጅረት ድል ፡ ከነሱት ፡ ጋር ፡ ተካፍሎ ፡ እርስት ምናለ ፡ ውበት ፡ ምናለ ፡ ፍሰሃ አንደመገኘት ፡ ከዚህ ፡ ክብር ፡ ጋር ሲያልፍ ፡ ፊተኛው ፡ ሰማይ ደግሞ ፡ አንደገና ፡ አዲስ ፡ ሰማይ ሲያበቃ ፡ ይሄኛው ፡ ምድር ዘላለም ፡ አለ ፡ የክብር ፡ ምድር
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.