Loading
በሰው ክፋት ማዕበል ምድር ስትናወጥ ፈጣሪ እንኳ በሰራው ፍጡር እስኪፀፀት የአንድ ኖህ ጎዳና አካሄድ ቢቀና የሰው ሕይወት አልቀጠለም ወይ እንደገና X2 በውሸት ከተማ እውነት እንግዳ ነው መስሎ ፀጉረ ልውጥ የሚያውቀው የሌለው እውነትን በተቀማ ትውልድ ማን ይሆን የእውነት ዘመድ ሁሉ ገሸሽ ሲል ለመስቀል ሲደራ ማን አብሮ ይዘልቃል ከባይተዋር ጋራ እንደ ውሃና ዘይት አይደሉም ወይ እውነት እና ሃሰት ምን አንዱ ቢበዛ መቼም አያብሩ ዘላለም በርቀት በጊዜ ፈተና ወደቅህ ሚለው የለም በእሳት ንዳድ አልፎ አመድ አያውቀውም በልዩነት መንገድ በሰላም ይተማል አጃቢ ሳያሻው ዘላለም ይኖራል X2 የዝምታው ድምፀት ከመብረቅ ጽኑ ነው አለት ከሚያነቃ ከሚሰነጥቀው እርሱ ተረጋግቶ አገር ይረበሻል የለህም የሚለው እንቅልፍ አጥቶ ያድራል ከብዙ ግርግር አባይ ከዋለበት እውነት ከሚመስል አሳች ከበዛበት ዘንድሮም ጉዳዩ ከእውነት ጋር ብቻ እውነት እና እውነት ከራሱ ጋር ብቻ በውሸት ከተማ እውነት እንግዳ ነው መስሎ ፀጉረ ልውጥ የሚያውቀው የሌለው እውነትን በተቀማ ትውልድ ማን ይሆን የእውነት ዘመድ ሁሉ ገሸሽ ሲል ለመስቀል ሲደራ ማን አብሮ ይዘልቃል ከባይተዋር ጋራ የታመነ ጓዳው ዮሴፍ ትንሹ ዛፍ ባልዋለበት ቢውል በእመቤቲቱ አፍ ከእመቤትስ በላይ ሹምስ ማንን ያምናል በሃጥዕ ዘመን ዘንድ ጻድቅ ወህኒ ይወርዳል ምንም ቢያልፍ ተሳቆ በሚያልፍ ባለ ጊዜ በማያልፍ ተጥሷል ደርሶ የእውነት ጊዜ በአደባባይ ቢያፍር እውነትን አነግሶ ክብሩም በአደባባይ ይሄው ተመልሶ ሃብት ነው ጌጥ እውነት ምን ባይሆን ለጊዜው ከርሞም ቢመነዘግ ከፋይ ለከፈለው እውነትን በተቀማ ትውልድ ማን ይሆን የእውነት ዘመድ ብርሃን ቃሉን ሲሰጥ ጨለማን ሲደክመው የእውነት ቤት ይደምቃል ለእግዚአብሔር ያደረው ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ X2 እውነት እግዚአብሔር ነው የማይለወጥ ጽኑ በሰልፍ ብዛት የማይደክመው ከበረታው በላይ ብርቱ ባህርይው ሰላም ነው አያምንም በሁከት ራሱን ለማሳመን አይገባም ከጭንቀት ህሊና ወዳጁ ጊዜ መፍቻ ቁልፍ ተረጋግቶ ይኖራል ተከፍቶ በስንቱ ጽኑ ጽኑ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.