Loading
ሩጫው ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ሰላምን ፡ ፍለጋ እርካታን ፡ ፍለጋ ሁሉም ፡ በየፊናው ፡ ሚለው ፡ ደፋቀና ሚለው ፡ ጎንበስ ፡ ቀና ገንዘብ ፡ ቁስን ፡ እንጂ ፡ እረፍት ፡ መች ፡ ይገዛል በየደረሰበት ፡ ሰው ፡ ሃሳብ ፡ ይገዛል ጭንቀት ፡ ይሸምታል እረፍት ፡ መገኛው ፡ ኢየሱስ ሰላም ፡ ማደሪያው ፡ ኢየሱስ ደስታ ፡ ሀገሩ ፡ ኢየሱስ እረፍት ፡ መኖሪያው ፡ ኢየሱስ ሀብት ፡ ጥሪት ፡ ይዞ ፡ የተትረፈረፈ ከእድሜ ፡ ልክ ፡ ያለፈ ሰላም ፡ ከሌለበት ፡ ሰላምን ፡ ፍለጋ ፡ ስንቱ ፡ ነው ፡ የዋለ የተንከራተተ ዛሬን ፡ እረፍት ፡ አጥቶ ፡ ለነገ ፡ ያልማል ነገም ፡ ነገን ፡ ሲቀርጽ ፡ ሳያልቅ ፡ ዘመን ፡ ያልቃል እረፍት ፡ መገኛው ፡ ኢየሱስ ሰላም ፡ ማደሪያው ፡ ኢየሱስ ደስታ ፡ ሀገሩ ፡ ኢየሱስ እርካታው ፡ መኖሪያው ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ በላው ፡ ጠጣው ፡ ትርፌ ፡ ምንድነው? አጌጥኩ ፡ ለበስኩ ፡ ትርፌ ፡ ምንድነው? ተማርኩ ፡ አወኩ ፡ ትርፌ ፡ ምንድነው? ምድር ፡ ሞላልኝ ፡ ትርፌ ፡ ምንድነው? ኸረ ፡ እኔ ፡ በእንጀራ ፡ ብቻ ፡ ኸረ ፡ አልኖርም ኸረ ፡ እኔ ፡ በምድሩ ፡ ብቻ ፡ ኸረ ፡ አልኖርም ክፍተቴ ፡ ሌላ ፡ ነው ፡ ጉድለቴ የማልሞላው ፡ በማንነቴ እሮጬ ፡ እሮጬ ፡ ትርፌ ፡ የእኔ ፡ ድካም ፡ ነው የነፍስ ፡ እርካታዬ ፡ ጌታ ፡ በአንተኮ ፡ ነው እንኳን ፡ ያንተ ፡ ሆንኩኝ ፡ አወኩህ ፡ እንኳን እንዳልችል ፡ ሆኛለሁ ፡ ለሌላ ፡ እንዳልሆን የማምነው ፡ እውነት ፡ በፍቅር ፡ ይዞኛል ሌላ ፡ ሌላ ፡ እንዳላይ ፡ ውስጤን ፡ ሞልተኸዋል አሰብኩት ፡ እራሴን ፡ ከአንተ ፡ ውጪ አሰብኩት ፡ ወጥቼም ፡ ከቤትህ ባዶ ፡ ነኝ ፡ ቅብዝብዝ ፡ የሌለኝ ፡ እረፍት እኔ ፡ አልችልም ፡ ሰው ፡ አልሆንም ፡ በሌለህበት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.