Loading
ውጣ ፡ ውረድ ፡ ቢበዛ ፡ እንኳን ፡ ቢጨንቀኝም ፡ ማደርገዉ አንተን ፡ ትቼ ፡ ሌላ ፡ አማራጭ ፡ መፈለግ ፡ አይሆንልኝም ውላችን ፡ አይደለም ፡ ስኬት ፡ ሳይሆንልኝ ፡ ግን ፡ ልርቅህ በደምህ ፡ የተዋጀሁት ፡ በቂዬ ፡ ነው ፡ ማንነትህ አዝ:- የወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ አከበርኩህ ፡ ጌታ ነፍሴም ፡ ተሰጥታለች ፡ ለአንተ ፡ ታዚም ፡ ሁሌም ፡ ጠዋት ፡ ማታ ቃልኪዳናችንም ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው አጋጣሚ ፡ አይደለምና ፡ ፍቅርህ ፡ ሁኔታ ፡ ላይ ፡ ያየሁህ አንለያይም (፰x) ሄድኩኝ ፡ ብለው ፡ ከሄዱበት ፡ አንዳች ፡ የለም ፡ የተረፈ ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ከሚጠፋው ፡ ከዚች ፡ ምድር ፡ ያለፈ ዛለዓለሜ ፡ ቤቴ ፡ የአንተ ፡ ይሁን ፡ ይህን ፡ እወዳለሁ በከንፈሬ ፡ ሳልበድልህ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ መርጫለሁ አዝ:- የወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ አከበርኩህ ፡ ጌታ ነፍሴም ፡ ተሰጥታለች ፡ ለአንተ ፡ ታዚም ፡ ሁሌም ፡ ጠዋት ፡ ማታ ቃልኪዳናችንም ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው አጋጣሚ ፡ አይደለምና ፡ ፍቅርህ ፡ ሁኔታ ፡ ላይ ፡ ያየሁህ አንለያይም (፰x) የአንተ ፡ ብሆን ፡ መታደሌ ፡ የጌታ ፡ ልጅ ፡ መባሌ ተጠርቼ ፡ መች ፡ ቀረሁኝ ፡ አባ ፡ በአንተ ፡ ተወደድኩኝ ምን ፡ አጥቼ ፡ ልሂድ ፡ ከአንተ ፡ ምን ፡ ጐድሎብኝስ ፡ ከእቅፍህ የእኔ ፡ ብዬ ፡ ምኖርበት ፡ መመኪያዬም ፡ ጌጤም ፡ ቤትህ አዝ:- የወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ አከበርኩህ ፡ ጌታ ነፍሴም ፡ ተሰጥታለች ፡ ለአንተ ፡ ታዚም ፡ ሁሌም ፡ ጠዋት ፡ ማታ ቃልኪዳናችንም ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው አጋጣሚ ፡ አይደለምና ፡ ፍቅርህ ፡ ሁኔታ ፡ ላይ ፡ ያየሁህ አንለያይም (፲፮x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.