Loading
ክበርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም ንገሥልኝ ፡ ብዬ ፡ በልቤ ፡ አልረካሁም ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ምትወደው ባቀርብልህ ፡ ጌታ ፡ ከምንም ፡ ባልሰለቸሁ (፪x) ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ሁሌ ፡ ከሚያከብሩህ እኔን ፡ ከመደብከኝ ፡ ከሚያመሰግኑህ ጥማቴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ አከብርሃለሁ በቀንም ፡ በሌሊት ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ አዝ፦ ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፪x) ሰማይና ፡ ምድር ፡ ክብርን ፡ ያወራሉ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እያሉ እኔም ፡ በተራዬ ፡ ለትውልድ ፡ ልናገር የሚመስልህ ፡ የለም ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ክበር አዝ፦ ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፪x) ፊትህን ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ መልሰሃልና የአንተ ፡ ወገን ፡ አርገህ ፡ ዋጅተኸኛልና ከምርጦችህ ፡ ጋራ ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ እሰግድልሃለሁ ፡ መቅደስህ ፡ ገብቼ አዝ፦ ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፪x) የምለው ፡ ብዙ ፡ አለኝ ፡ ስላንተ ፡ ማወራው አምላኬ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የምናገረው የሚሰማኝና ፡ የሚያየኝ ፡ ያክብርህ የእኔ ፡ ብቻ ፡ አይበቃም ፡ ዘሬም ፡ ይገዛልህ ክበርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም ንገሥልኝ ፡ ብዬ ፡ በልቤ ፡ አልረካሁም ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ምትወደው ባቀርብልህ ፡ ጌታ ፡ ከምንም ፡ ባልሰለቸሁ (፪x) አዝ፦ ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.