Loading
እኔ ፡ እንደው ፡ ልማዴ ፡ ነው ፡ ሳይነጋ ፡ መዘመር እኔ ፡ እንደው ፡ ልማድ ፡ አለኝ ፡ ችግር ፡ ፊት ፡ መዘመር ስላንተ ፡ ሲወራ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኝ ፡ ጀመር ሁሉ ፡ ደህና ፡ ነው ፡ ስል ፡ ደህና ፡ ሆኖ ፡ ቀረ አስፈሪው ፡ ተራራ ፡ ሆነ ፡ እንዳልነበረ ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ ልበልህ ፡ ጌታዬ /3×/ ልበልህ ፡ ንጉሴ /3×/ ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ የዕለቱን ፡ መስዋዕት ፡ ከእኔ ፡ የሚሻው ላሳርግለት ፡ ያውድ ፡ መዓዛው አያፍርም ፡ ፊቴ ፡ እርሱ ፡ ጋ ፡ ደርሶ ይለውጠዋል ፡ ሁሉን ፡ አድሶ ጥያቄ ፡ ኖሮ ፡ ያልተመለሰ መዘመር ፡ አልተው ፡ ፍቅሬም ፡ አልቀነሰ ማጠኛውን ፡ ስጡኝ ፡ የተራዬን ፡ ልበል እኔ ፡ ጋር ፡ ደርሶ ፡ አምልኮ ፡ አይጓደል ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ ላስተዋለውማ ፡ ተፈጥሮም ፡ ያወራል ሊነጋጋ ፡ ሲቀርብ ፡ እጅግ ፡ ይጨልማል ምልክት ፡ ነበር ፡ ድቅድቅ ፡ ማለቱ የመጎብኛዬ ፡ ደረሰ ፡ ሰዓቱ ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ ልበልህ ፡ ጌታዬ /3×/ ልበልህ ፡ ንጉሴ /3×/ ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.