Loading
ስለበደላችን ፡ ደቀቀ ስለኃጥያታችን ፡ ቆሰለ ስለመተላለፋችን ፡ ሞተ በመገረፉ ፡ ቁስል ፡ ፈወሰን በቀራኒዮው ፡ ስፍራ ፡ በመስቀል ፡ የሞተው በእሾህ ፡ ሲጎነጉኑ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው በጦር ፡ ጎኑን ፡ ሲሉ ፡ በአለንጋ ፡ ሲልጡ ዝም ፡ ማለቱ ፡ ለእኛ ፡ ነው ፡ መራራን ፡ ሲያጠጡ ፍጹም ፡ አላፈረም ፡ እርቃኑን ፡ ሲታይ ፡ ሰለ ፡ እኛ ፡ ለአለም ስሙ ፡ ይክበር ፡ ዘላለም ፡ ይንገስ ፡ ወልድ ፡ እግዚአብሄር በእራስ ፡ ቅሉ ፡ መንደር ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ ፡ ንጹህ ፡ ነው ያለዋኖስ ፡ ያለበጐች ፡ ደም ፡ የአለምን ፡ በደል ፡ ጠረገው ደሙን ፡ ይዞ ፡ ገባ ፡ ወደ ፡ አባቱ ፡ አወረደ ፡ ከላይ ፡ ምሕረቱን አመጻችን ፡ ሁሉ ፡ ተወግዶ ፡ ተቆጠረ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ፅድቁ ፍጹም ፡ አላፈረም ፡ እርቃኑን ፡ ሲታይ ፡ ሰለ ፡ እኛ ፡ ለአለም ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ዘላለም ፡ ይንገስ ፡ ወልድ ፡ እግዚአብሄር እጅጉን ፡ በችንካር ፡ አጥብቀው ፡ ወጠሩ ጀርባውን ፡ በጅራፍ ፡ እያቆሰሉ የአለማት ፡ ፈጣሪን ፡ ያለእፍረት ፡ ቢንቁ ጸሀይ ፡ እና ፡ ጨረቃ ፡ እርሱን ፡ አከበሩ በምሕረቱ ፡ ነው ፡ ባለጠጋ እኛን ፡ ሊምር ፡ ወደደ ፡ ጌታ እኛን ፡ አለ ፡ ሩሃማ (፪x) እኔን ፡ አለ ፡ ሩሃማ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.