Loading
ተመርጫለው ፡ እኔ ተወድጃለው ፡ እኔ ፀድቄአለው ፡ በእርሱ እንድኖርለት ፡ ለእርሱ (፪x) ፀጋው ፡ በእምነት ፡ አድኖኝ ኢየሱስ ፡ ጽድቁን ፡ አልብሶኝ ስለኔ ፡ በአብ ፡ ፊት ፡ ታይቶ ፈጽሞታል ፡ ሥራዬን ፡ ጨርሶ (፪x) ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ፀጋው ፡ አቁሞኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ምህረቱ ፡ አኑሮኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ቸርነቱ ፡ በዝቶልኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ስግደት ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ልዕልና ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ይገባዋል ገና ፡ ከፍጥረት ፡ በቁጣ ፡ ነበርኩኝ በበደሌ ፡ ምክንያት ፡ ሙት ፡ የሆንኩኝ በኃጢአቴ ፡ መብዛት ፡ ሙት ፡ የሆንኩኝ (፪x) ግን ፡ በምህረቱ ፡ ባለጠጋ ፡ ስለሆነ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ለእኔ ፡ አደለ ግን ፡ በምህረቱ ፡ ባለጠጋ ፡ ስለሆነ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ለእኔ ፡ እንኪ ፡ አለ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ፀጋው ፡ አቁሞኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ምህረቱ ፡ አኑሮኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ቸርነቱ ፡ በዝቶልኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ስግደት ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ልዕልና ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ይገባዋል
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.