Loading
አብልጬ/አብዝቼ ፡ እንድወድህ አብዝቼ/አብልጬ ፡ እንዳፈቅርህ አንተን ፡ ከመካድ ፡ ይልቅ ፡ እራሴን ፡ እንድክድ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ እኔ ፡ እንኳን ፡ በአቅሜ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነኝ ሞት ፡ ቢሆን ፡ እስራት ፡ አንተን ፡ ለሚያገኝህ እኔ ፡ እራሴን ፡ እሰዋለሁ ፡ ከአንተ ፡ አይበልጥብኝም ብሎ ፡ ፊትህ ፡ እንዳላለ ፡ በገረድ ፡ ፊት ፡ ካደህ ፀጋህ/ኃይልህ ፡ ዳግም ፡ አቆመና ፡ ስለአንተ ፡ መስካሪ/ሰባኪ ፡ አረገው ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ እኔ ፡ እንኳን ፡ በአቅሜ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነኝ ብዙ ፡ ፍቅርን ፡ መግለጥ ፡ በአፌ ፡ መቻሌ ለተግባር ፡ ፈጥኜ/ቸኩዬ ፡ ግን ፡ አንተን ፡ መካዴ ከአንተ ፡ ያነሰን ፡ ነገር ፡ ማድነቄ ፡ ቀርቶ እንድወድህ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ አብዝቶ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ እኔ ፡ እንኳን ፡ በአቅሜ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነኝ ውድህ ፡ ያረከኝን ፡ አንተን ፡ ውዴ ፡ እንዳደርግህ ከነፍስህ/ከክብርህ ፡ በላይ ፡ የወደድከኝን ፡ እንድወድህ ጸጋህ/ሀይልህ ፡ በረዳኝ ፡ መጠን ፡ እንድቀርብህ እኔም ፡ እሻከሁ ፡ የእውነቴን ፡ ልወድህ/ልመስልህ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ፀጋህ ፡ ይርዳኝ እኔ ፡ እንኳን ፡ በአቅሜ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነኝ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.