Loading
እንደኔማ ፡ ቢሆን ፡ አልቆልኝ ፡ ነበረ የበደሌ ፡ ብዛት ፡ እየተቆጠረ ጌታዬ ፡ ግን ፡ አምላኬ ፡ ግን ፡ ዕዳዬን ፡ አስቀረ (፪x) በዘለዓለም ፡ ሥሙ ፡ ቃልኪዳን ፡ ገባልኝ አንቺ ፡ ልጅ ፡ በሕይወት ፡ ትኖሪያለሽ ፡ አለኝ ጌታዬ ፡ ነው ፡ አዳኜ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ እወደዋለሁ (፪x) የኃጥያቴ ፡ ቀንበር ፡ ከብዶ ፡ እያስጨነቀኝ ከሰው ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ነጥሎ ፡ እያስቀረኝ ጌታዬ ፡ ግን ፡ አምላኬ ፡ ግን ፡ ፈልጐ ፡ አገኘኝ (፪x) ያደረኩትን ፡ ሁሉ ፡ የልቤን ፡ ነገረኝ ኃጥያቴን ፡ ሻረና ፡ ከሰው ፡ ቀላቀለኝ አምላኬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ (፪x) ዳግም ፡ ላልጠማ ፡ ቀንበር ፡ ላይጫነኝ ከጨለማው ፡ ሰፈር ፡ ጠርቶ ፡ አወጣኝ ጌታዬ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ (፪x) ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ ፡ እኔ ፡ ዝም ፡ አልልም የተረደገልኝ ፡ ዝም ፡ አያሰኘኝም ኢየሱስ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው ጌታዬ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ እገዛለታለሁ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.