Loading
አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ የውስጥ ፡ ብሶቴን ፡ ጭንቄን ፡ ሚያሟላ እድል ፡ ፈንታዬ ፡ አንተው ፡ ነህና አዋይሃለሁ ፡ አጫውትሃለሁ ማን ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ (፪x) ዞሬያለሁኝ ፡ በዓለም ፡ ተስፋ ፡ አገኝ ፡ መስሎኝ በከንቱ ፡ ዘመኔን ፡ እንዲያው ፡ ጨረስኩኝ የምታዛልቀኝ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ ነህ ተረድቻለሁ ፡ ና እምባዬን ፡ አብስ ፡ ተስፋዬን ፡ አድስ ከማህጸን ፡ ጀምሮ ፡ ተሸክመኸኛል እንደ ፡ ልጅ ፡ አባብለህ ፡ አሳድገኸኛል ከአንተ ፡ ወዲያ ፡ ለእኔ ፡ የለኝም ፡ የማውቀው ኧረ ፡ ፊትህ ፡ ወድቄ ፡ እማጸንሃለሁ ጌታ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ ጌታ ፡ አለሁልህ ፡ በለኝና እስኪ ፡ ልረፍ ፡ ድምጽህን ፡ ልስማ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ መጠጊያዬን ፡ አውቃለሁ አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ የውስጥ ፡ ብሶቴን ፡ ጭንቄን ፡ ሚያሟላ እድል ፡ ፈንታዬ ፡ አንተው ፡ ነህና አዋይሃለሁ ፡ አጫውትሃለሁ ማን ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ (፪x) ወደ ፡ ቀኝ ፡ ወደ ፡ ግራ ፡ ተመለከትኩኝ ተስፋ ፡ የሚሆነኝ ፡ አንድም ፡ አጣሁኝ መሸሸጊያዬ ፡ ለእኔ ፡ መድሃኒት ለነፍሴ ፡ ጌታ ፡ ና ከእስራት ፡ ፍታኝ ፡ ልጄ ፡ ነህ ፡ በለኝ ብዙ ፡ ነገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ የማጫውትህ የልቤን ፡ የውስጤን ፡ ሁሉንም ፡ ልንገርህ ፡ ኢየሱስ ነፍሴ ፡ በእጅህ ፡ ናት ፡ መላው ፡ አካላቴ ፈቃድህ ፡ ይሁንልኝ ፡ ያልከው ፡ በሕይወቴ ጌታ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ ጌታ ፡ አለሁልህ ፡ በለኝና እስኪ ፡ ልረፍ ፡ ድምጽህን ፡ ልስማ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ መጠጊያዬን ፡ አውቃለሁ አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ የውስጥ ፡ ብሶቴን ፡ ጭንቄን ፡ ሚያሟላ እድል ፡ ፈንታዬ ፡ አንተው ፡ ነህና አዋይሃለሁ ፡ አጫውትሃለሁ ማን ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.