Loading
ከአንተ ፡ ወደ ፡ ማን ፡ እሄዳለሁ ፡ ማን ፡ አላት ፡ ነፍሴ ለሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ አንተ ፡ አይደለህ ፡ ወይ ፡ ክብሬ ፡ ሞገሴ ያለአንተ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ ከውኃ እንደወጣ ፡ ዓሣ ፡ ያኔ ፡ እጠፋለሁ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መኖር ፡ ይሻለኛል ሕይወቴ ፡ ነህ ፡ አልፈልግም ፡ ላጣህ ፡ አንተን ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መኖር ፡ ይሻለኛል ሰላሜ ፡ ነህ ፡ አልፈልግም ፡ ላጣህ ፡ አንተን ዋናዬ ፡ ነህ ፡ ዋናዪ ፡ ነህ ፡ እኔስ ፡ አልጣህ ዋናዬ ፡ ነህ ፡ ዋናዬ ፡ ነህ ፡ እኔስ ፡ አልጣህ በሰፈሬ ፡ በመንደሬ ፡ ድል ፡ ልትሰጠን ፡ ስትመጣ ጉብኝትህ ፡ እንዳያልፈኝ ፡ በስፍራዬ ፡ እንዳልታጣ ጠብቅሃለሁ ፡ ተሰናድቼ ፡ ቤቴን ፡ መንደሬን ፡ አጸዳድቼ ጠብቅሃለሁ ፡ ተሰናድቼ ፡ ቤቴን ፡ መንገዴን ፡ አጸዳድቼ ጠብቅሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ተሰናድቼ ቤቴን ፡ ጓዳዬን ፡ አሃ ፡ አጽዳድቼ (፪x) አምላኬ ፡ ፊትህን ፡ እሻለሁ ፡ በዚህ ፡ ቦታ እንድትዳስሰኝ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ አትለፈኝ ፡ ጌታ ፡ አትለፈኝ ፡ ጌታ አትለፈኝ ፡ ኦሆ ፡ አትለፈኝ ፡ ኦሃ አትለፈኝ ፡ አባ ፡ አትለፈኝ ፡ ኦሆ ጌታ ፡ ጌታ ፡ አትለፈኝ ፡ አትለፈኝ ጸሎቴ ፡ ጩሄቴ ፡ ሞገስ ፡ ያግኝህ ፡ ሞገስ ፡ ያግኝህ አትለፈኝ ፡ አትለፈኝ ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ሕይወት ፡ ሕይወት ፡ የለኝም አትተወኝ ፡ አትተወኝ ፡ ያለአንተ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ አዎ ልቤ ፡ እያወቀው ፡ መውደቅ ፡ መሸነፌን የግብዝነቴ ፡ ታገለው ፡ መንፈሴ አስመስሎ ፡ መኖር ፡ በቃ ፡ ይበቃኛል ለውጠኝ ፡ አባቴ ፡ ሕይወት ፡ ይሻለኛል ይሻለኛል ፡ ሕይወት ፡ ይሻለኛል (፪x) አትለፈኝ ፡ ኦሆ ፡ አትለፈኝ ፡ ኦሆ ሽንገላ ፡ ተሞልቶ ፡ አቤት ፡ አንደበቴ ጉልበቴን ፡ ጨረስኩት ፡ ባዶ ፡ ሆነ ፡ ቤቴ ያው ፡ ከነድካሜ ፡ ፊትህ ፡ ወድቄያለሁ ለፈቃዴ ፡ አትስጠኝ ፡ እለመንሃለሁ ሁሉን ፡ ልጣ ፡ አንተን ፡ ከማጣ ፡ አባ ፡ አንተን ፡ ከማጣ ሁሉ ፡ ይቅር ፡ አንተ ፡ ከምትቀር ፡ አባ ፡ አንተ ፡ ከምትቀር (፪x) አንተው ፡ ትሻለኛለህ አንተው ፡ ትበቃኛለህ ነፍሴን ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቻለሁ አባ ፡ ተማርኬያለሁ ተማርኬያለሁ ፡ ተማርኬያለሁ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.