Loading
ሠማይን ዘርግተህ እንዲህ አንጣለሃል ከትልቅነቱ ብዛት የሰው ስሌት ያልፋል አንተ የሰራኸው በስንዝር የለካኸው ይህ ሰማይ ትልቅ ከተባለ አንተ ምን ትባላለህ አዝ፦ ከሰማያት በላይ በላይ ከምድርም በላይ በላይ ከፍጥረታት በላይ በላይ አንት ትልቅ ነህ አንት ትልቅ ነህ (3x) በምድር የሰው ቁጥር እጅጉን ብዙ ነው ከአዳም ጀምሮ እስካሁን የኖረው በፊት ይህ ሁሉ ሲታይ የእኔ ጌታ በገንቦ እንዳለች ትንሽ ጠብታ ምትገርም ነህ ጌታ አዝ፦ ከሰማያት በላይ በላይ ከምድርም በላይ በላይ ከፍጥረታት በላይ በላይ አንት ትልቅ ነህ አንት ትልቅ ነህ (3x) በምድር ለሚኖሩ ምድር ሰፊ እርስት ናት ስፋቷን በብዙ ቁጥር የሚያሰሏት አንተ ግን ጌታዬ ትልቅ ትልቅ ነህ በክበቦቿ ላይ ትቀመጣለህ ከፍ ከፍ ላድርግህ አዝ፦ ከሰማያት በላይ በላይ ከምድርም በላይ በላይ ከፍጥረታት በላይ በላይ አንት ትልቅ ነህ አንት ትልቅ ነህ (5x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.