Loading
የምድር ፡ ዳርቻዎች ፡ ፈጣሪ ውሆችን ፡ በእፍኝህ ፡ የሰፈርህ ሰማየ ፡ ሰማያት ፡ የአንተ ፡ ናቸው በግርማዊነትህ ፡ ሰራሃቸው ጥንት ፡ የነበርህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ ለዘለአለም ፡ የምትኖር (፪x) አዝ፦ አንተ ፡ ዘለአለም ፡ ነህ (፪x) ጅማሬና ፡ ፍጻሜ ፡ የሌለህ ጌታ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፪x) ሰማይና ፡ ምድር ፡ በስፍራቸው ሳይኖሩ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ቀድመሃቸው ጅማሬ ፡ የለህም ፡ ፍጻሜ እድሜህ ፡ አይሰላ ፡ ሰው ፡ አይደለህ ጥንት ፡ የነበርህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ ለዘለአለም ፡ የምትኖር (፪x) አዝ፦ አንተ ፡ ዘለአለም ፡ ነህ (፪x) ጅማሬና ፡ ፍጻሜ ፡ የሌለህ ጌታ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፪x) ከአማልክት ፡ መሃከል ፡ እንደአንተ ፡ ማን ፡ ነው የእኔን ፡ ጌታ ፡ እግዚኣብሔር ፡ የሚመስለው አምላኬ ፡ ከሁሉም ፡ ትለያለህ አንተ ፡ የአማልክት ፡ ሁሉ ፡ አምላክ ፡ ነህ ጥንት ፡ የነበርህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ ለዘለአለም ፡ የምትኖር (፪x) አዝ፦ አንተ ፡ ዘለአለም ፡ ነህ (፪x) ጅማሬና ፡ ፍጻሜ ፡ የሌለህ ጌታ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.