Loading
የመውደዴን ፡ ብዛት ፡ የፍቅሬንም ፡ ብዛት በውስጤ ፡ ያለውን ፡ የንዳዱን ፡ ብርታት የማረከኝን ፡ የተረታሁልህን ልገልጠው ፡ አልችልም ፡ አንተ ፡ ያረክልኝን (፪x) አሸንፈኸኛል ፡ እመሰክራለሁ ጌታ ፡ አፌን ፡ ሞልቼ ፡ እናገራለሁ (፪x) የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ውስጤ ፡ ያለው እየጨመረ ፡ የሚሄድ ፡ ወንዝ ፡ ነው አሁንስ ፡ አየሁ ፡ ይህ ፡ ገብቶኛል የማልወጣው ፡ ነገር ፡ ይዞኛል (፫x) የምልህ ፡ አለኝ ፡ የምልህ ቋንቋን ፡ አጥቼ ፡ ያኖርኩልህ ቃላት ፡ አግኝቼ ፡ መጥቻለሁ ኢየሱስዬ ፡ ወድሃለሁ (፪x) ኧረ ፡ ማን ፡ ሊተካህ ፡ አንተን (፪x) ስፍራህን ፡ የሚወስድ ፡ ከወዴት ፡ ሊገኝ በሰማይ ፡ የለም ፡ በምድርም ፡ የለም ከምድርም ፡ በታች ፡ አይገኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.