Loading
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x) አዝ፦ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ! የስምህ ፡ ሥልጣን ፡ ታላቅ ፡ ነው! (፬x) ከጣዖታት ፡ ዘንድ ፡ ፊቴን ፡ አዙሬ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ሆነልኝ ፡ መዝሙሬ ስል ፡ "አንተ ፡ እና ፡ ስምህ ፡ ታላቅ ፡ ነው!" ሌላ ፡ ቃላት ፡ መግላጫ ፡ ባጣ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ የስምህ ፡ ሥልጣን ፡ ታላቅ ፡ ነው (፬x) ቢሰለፉ ፡ አማልክት ፡ በተርታ ካንዳቸውም ፡ መሳይ ፡ የለ ፡ ጌታ እንደ : ስምህ: ነህ ፡ የሁሉ ፡ ገዢ ዘመንህ ፡ ዕድሜህ ፡ አይባልም ፡ ከዚህ ልክ ፡ የለህም ፡ ወሰን ፡ የለህም ልክ ፡ የለህም ፡ መጠን ፡ የለህም በሰው ፡ ቋንቋ ፡ ከቶ ፡ አልገልጥህም (፪x) ስምህ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ለጠራው ፡ ሁሉ ፡ 'ሚሆን ፡ መዳኛ ስምህ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ለደካከመው ፡ ብርታት ፡ ማግኛ አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ በምንም ፡ ነገር ፡ ከቶ ፡ አትለካም አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ዘመንህ ፡ አያልቅም ፡ የለብህ ፡ ድካም
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.