Loading
ምን ፡ እላለሁ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁኝ ምን ፡ እላለሁኝ ፡ መነ ፡ እላለሁኝ ስትረዳኝ ፡ እያየሁ ፡ ስታግዘኝ ፡ ስታግዘኝ ፡ ስታግዘኝ የቱን ፡ ዘምሬ ፡ የቱን ፡ እተዋለሁ ለኔ ፡ ያረክልኝ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ለኔ ፡ ያረክልኝ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው መልካም ፡ ነህ ፡ ቢሉህ ፡ መልካምነትስ ፡ መቼ ፡ ይገልጽሃል ፍቅር ፡ ነህ ፡ ቢሉህ ፡ የፍቅር ፡ ልኩ ፡ መቼ ፡ ይገልጽሃል ኧረ ፡ ማን ፡ ልበልህ ፡ ማን ፡ ልበልህ ፡ ቃል ፡ አጣሁልህ ከተጣልኩበት ፡ አዘቅት ፡ መጥተህ ከጠላቴ ፡ እጅ ፡ እኔን ፡ ተናጥቀህ በደምህ ፡ ገዝተህ ፡ የአንተ ፡ ካረከኝ እነዴት ፡ አልዘምር ፡ እንዴት ፡ አልቀኝ ዛሬማ ፡ በላይ ፡ ሆኖአል ፡ ስፍራዬ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ ሆኖአል ፡ መቀመጫዬ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ ይድረስህ እድሜ ፡ ዘመኔን ፡ ልዘምርልህ እንዴት ፡ ላመስግንህ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ላወድስህ ከቃላት ፡ በላይ ፡ ነፍሴን ፡ አፍስሼ ሁለንተናዬን ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ በፍቅርህ ፡ ጉልበት ፡ ተረትቻለሁ ይኽው ፡ ላመልክህ ፡ መጥቻለሁ መልካም ፡ ነህ ፡ ቢሉህ ፡ መልካምነትስ ፡ መቼ ፡ ይገልጽሃል ፍቅር ፡ ነህ ፡ ቢሉህ ፡ የፍቅር ፡ ልኩ ፡ መቼ ፡ ይገልጽሃል ኧረ ፡ ማን ፡ ልበልህ ፡ ማን ፡ ልበልህ ቃል ፡ አጣሁልህ ሙት ፡ የነበርኩኝ ፡ በበደል ፡ ብዛት ሕያው ፡ አረከኝ ፡ ነፍሴን ፡ ቀደስካት ከክርስቶስ ፡ ጋር ፡ ሕይወት ፡ ሰጠኽኝ በትልቅ ፡ ፍቅርህ ፡ እንዲያው ፡ ወደድከኝ ጽድቄ ፡ ነህና ፡ ቅድስናዬ ፡ እንከን ፡ የሌለህ ፡ ንጽህናዬ ፡ ብቃት ፡ የለኝም ፡ የምለው ፡ የእኔ ቤዛ ፡ ባትሆነኝ ፡ አንተ ፡ መድኅኔ እንዴት ፡ ላመስግንህ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ላወድስህ ከቃላት ፡ በላይ ፡ ነፍሴን ፡ አፍስሼ ሁለንተናዬን ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ በፍቅርህ ፡ ጉልበት ፡ ተረትቻለሁ ይኽው ፡ ላመልክህ ፡ መጥቻለሁ አመልክሃልሁ ዘላለሜ ፡ ኢየሱሴ ፡ የእንተ ፡ ነው አመልክሃለው የእኔ ፡ ጌታ ፡ ዘመኔን ፡ ውረሰው ዘመኔ ፡ የአንተ ፡ ነው ኑሮዬ ፡ የአንተ ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.