Loading
ለእኔስ ፡ ሕይወት ፡ በዝቶልኛል ፣ ሕይወት ፡ በዝቶልናል ኢየሱሴ ፡ መዳኛ ፡ ማምለጫም ፡ ሆኖኛል ኢየሱሴ ፡ መዳኛ ፡ ማምለጫም ፡ ሆኖኛል (፪x) ሰው ፡ ሁሉ ፡ እንደመሰለው ፡ ቢያወራ ፡ ብዙ ፡ ቢናገር ለእኔ ፡ ግን ፡ የገባኝ ፡ እውነት ፡ አረገኝ ፡ በዚያው ፡ እንድቀር ለዚህ ፡ ነው ፡ እምቢ ፡ ማለቴ ፡ ሳይገደኝ ፡ ወጣትነቴ የዓለምን ፡ ግብዣዋን ፡ ንቄ ፡ ወገቤን ፡ ትጥቄን ፡ ማጥበቄ አዝ፦ አያምረኝም ፡ ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ነገ ፡ ሚጠፋ አያምረኝም ፡ የዓለም ፡ ክብር ፡ ጊዜያዊ ፡ ተስፋ አያምረኝም ፡ ይሄ ፡ አይደለም ፡ ለእኔማ ፡ ክብሬ መኖር ፡ እንጂ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ እርሱን ፡ አክብሬ (፪x) ለእኔስ ፡ ሕይወት ፡ በዝቶልኛል ፣ ሕይወት ፡ በዝቶልናል ኢየሱሴ ፡ መዳኛ ፡ ማምለጫም ፡ ሆኖኛል ኢየሱሴ ፡ መዳኛ ፡ ማምለጫም ፡ ሆኖኛል (፪x) ትውልዱ ፡ ግራ ፡ ቢገባው ፡ የዘፈን ፡ ማዕበል ፡ ቢውጠው ነጐደ ፡ ፍጥረት ፡ ተሰዶ ፡ ገንዘብን ፡ ዓለምን ፡ ወዶ ቀን ፡ ሲመሽ ፡ ሌቱ ፡ ሲነጋ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ ፡ ለቤ ፡ እንዳይሰጋ የሰማይ ፡ ደጆች ፡ ተከፍተው ፡ የአምላኬን ፡ ውበት ፡ አያለው አዝ፦ አያምረኝም ፡ ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ነገ ፡ ሚጠፋ አያምረኝም ፡ የዓለም ፡ ክብር ፡ ጊዜያዊ ፡ ተስፋ አያምረኝም ፡ ይሄ ፡ አይደለም ፡ ለእኔማ ፡ ክብሬ መኖር ፡ እንጂ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ እርሱን ፡ አክብሬ (፪x) የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ የዘለዓለም (፪x) ሙሉ ፡ ልቤ ፡ ያረፈብህ የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ የዘለዓለም (፪x) ግራ ፡ ቀኙን ፡ እንዳላየው የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ የዘለዓለም (፪x) አንዴ ፡ ልቤን ፡ የማረከው የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ የዘለዓለም (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.