Loading
በዘመናት ፡ . (1) . ፡ ግን ፡ አላረጀህም የዓመታት ፡ እርዝማኔ ፡ አላታከተህም ትናንት ፡ ዛሬ ፡ ለዘለዓለም ፡ አንተ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ኃያል ፡ ንጉሥ ፡ እግዚአብሔር ፡ የምትገርም ፡ አምላክ ፡ ነህ (፭x) እንኳን ፡ አመለኩህ ፡ አንኳን ፡ ሰገድኩልህ ገናም ፡ አልበቃኝም ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ አዲስ ፡ ምሥጋና (፬x) ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ (፭x) ማልጄ ፡ ልዘምር ፡ ደግሞም ፡ ቀን ፡ በቀትር ምሽትም ፡ ጨምራለሁ ፡ ይኼም ፡ ሲያንስህ ፡ ነው (፪x) ምሥጋናዬ ፡ አይነስህ ፡ ይደራረብ ፡ በመቅደስህ (፪x) ብዙ ፡ አማልክት ፡ ወድቀዋል ፡ ለጥቂት ፡ ተደንቀው(?) መታሰቢያ ፡ እንኳን ፡ አጥተዋል ፡ ዘመን ፡ አልፎባቸው አንተ ፡ ግን ፡ እንዳማረብህ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ነህ ኃያል ፡ ንጉሥ ፡ እግዚአብሔር ፡ እጅግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነህ (፭x) እንኳን ፡ አደነኩህ ፡ እንኳን ፡ ሰገድኩልህ ገናም ፡ አልበቃኝም ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ አዲስ ፡ ምሥጋና (፭x) ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ (፭x) በታላላቅ ፡ ጉባኤ ፡ በጓዳም ፡ ለብቻዬ መስዋዕቴ ፡ ያርግልህ ፡ ጣፋጭ ፡ መዓዛ ፡ ይሁንልህ (፪x) አምልኮዬ ፡ አደነልህ ፡ ይደራረብ ፡ በመቅደስህ (፪x) ፍቅር ፡ ምህረት ፡ ቸርነትህ ፡ ማልዶ ፡ ማልዶ ፡ አዲስ ፡ ነው አሮጌ ፡ ታሪክ ፡ የለህም ፡ ብርታትህም ፡ ያው ፡ ነው የቅድስናህም ፡ ክብር ፡ እያደር ፡ ይደምቃል ኃያል ፡ ንጉሥ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዝናህ ፡ ምድርን ፡ ሞልቷል (፭x) እንኳን ፡ አወደስኩህ ፡ እንኳን ፡ ዘመርኩልህ ገናም ፡ አልበቃኝም ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ አዲስ ፡ ምሥጋና (፭x) ፡ ዛሬም ፡ ይኸውልህ (፬x) ካየሁት ፡ ከሰማሁት ፡ ለነፍሴ ፡ የቀረላት በአንተ ፡ መደነቅ ፡ ነው ፡ ዋናም ፡ ትርፍም ፡ የሆነላት (፪x) ምሥጋናዬ ፡ አይነስህ ዝማሬ ፡ አይነስህ አምልኮዬ ፡ አይነስህ አክብሮት ፡ አይነስህ ይደራረብ ፡ በመቅደስህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.